Tender Detail

Tender Details


በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ባ/ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ግዥ፣ የአየር ትራንስፖርት የዕቃና ሰነድ የማጓጓዝ አገልግሎት ግዥና የግማሽ ሊትር ውሃ ግዥ በዓመታዊ ውል ለመግዛት ስለሚፈለግ በዘርፍ ከተሰማሩ አካላት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 02/2018

 

በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ባ/ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ግዥ፣ የአየር ትራንስፖርት የዕቃና ሰነድ የማጓጓዝ አገልግሎት ግዥና የግማሽ ሊትር ውሃ ግዥ በዓመታዊ ውል ለመግዛት ስለሚፈለግ በዘርፍ ከተሰማሩ አካላት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ጨረታውን መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች /አቅራቢዎች/ ከዚህ በታች የተጠየቁትን መስፈርቶችና ግዴታዎች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል የታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ 2000 ብር በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፣
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አልካን ኮሌጅ ጎን ከሚገኘው ህንፃ ቢሮ ቁጥር 305 100 /አንድ መቶ ብር/ በመያዝ ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በጥንቃቄ በመሙላትና በሚገባ በማሸግ እንዲሁም በዋጋ መሙያው ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በግልጽ በማስቀመጥ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስሪያ ቤቱ የግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 304 ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፤ ነገር ግን 16ኛው ቀን በዓል ፣ እሁድ/ ከሆነ በ17ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል ።
  8. የጨረታ አሸናፊው የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና 50,000 /ሀምሳ ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ (specification) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ያገኛሉ፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ተጫራቾች የሚሞሉትን ሰነድ ኦሪጅናል /ዋና/ እና ኮፒ /ቅጅ/ ለየብቻ በማሸግ በድጋሚ በአንድ ፖስታ ሁለቱን በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

 

በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር የባ/ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

 

 

 

Save Tender