በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ባ/ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለሰራተኞች ጠዋት እና ማታ ከቤት ወደ ስራ ቦታ እና ከስራ ቦታ ወደ ቤት የትራንስፖርት አገልግሎት ለመግዛት ስለሚፈለግ በዘርፍ ከተሰማሩ አካላት ማለትም /7 1113/ የንግድ ስራ ፈቃድ የየብስና ተዛማጅ አገልግሎት ሆኖ ሊብሬው ለንግድ የሚውል እና /71112/ የንግድ ስራ ፈቃድ አገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሆኖ ሊብሬው የመኪና ማከራየት የሚል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 03/2018
በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ባ/ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለሰራተኞች ጠዋት እና ማታ ከቤት ወደ ስራ ቦታ እና ከስራ ቦታ ወደ ቤት የትራንስፖርት አገልግሎት ለመግዛት ስለሚፈለግ በዘርፍ ከተሰማሩ አካላት ማለትም /7 1113/ የንግድ ስራ ፈቃድ የየብስና ተዛማጅ አገልግሎት ሆኖ ሊብሬው ለንግድ የሚውል እና /71112/ የንግድ ስራ ፈቃድ አገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሆኖ ሊብሬው የመኪና ማከራየት የሚል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተጠየቁትን መስፈርቶችና ግዴታዎች ማሟላት ይጠበቅባችኋል።
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የባለቤትነት ማስረጃ ወይም ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል የታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 03 አልካን ኮሌጅ ጎን ከሚገኘው ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በጥንቃቄ በመሙላትና በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ በማሸግና በዋጋ መሙያው ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በግልጽ በማስቀመጥ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የግዥ ቢሮ ቁጥር 304 ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል ነገር ግን 16ኛው ቀን በዓል/እሁድ ከሆነ በ17ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል ።
- የጨረታ አሸናፊው የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና 10% በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የዓመቱን በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ በጨረታው የተገለፀውን አገልግሎት ብዛት እንዲገዛ አይገደድም።
- ተጫራቾች የሚሞሉትን ሰነድና ሌሎች ማስረጃዎች ኦሪጅናል /ዋና/ እና ኮፒ/ቅጅ ለየብቻ በማሸግ በድጋሚ በአንድ ፖስታ ሁለቱን በማሸግ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ከትራንስፖርት አገልግሎት ክፍያ ውጭ ማንኛውንም ወጭ ተቋሙ የማይሸፍን መሆኑን (የነዳጅ፣ የሹፌር እና የመኪና ብልሽት) መገንዘብ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
- ተቋሙ የሚፈልገው የትራንስፖርት አገልግሎት ሲሆን አገልግሎቱ ጠዋት የመግቢያ የስራ ስዓት እና ምሽት የስራ ሰዓት መውጫ ብቻ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች አንድ ሊብሬ/መኪና ከአንድ የጉዞ መስመር በላይ መጫረት የማይችሉ መሆኑን ማወቅ ይገባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-226-34-01/058-226-33-21
በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር የባ/ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
