Tender Detail

Tender Details


በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ በ2018ዓ/ም የስራ ዘመን የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን፣ አላቂ የፅዳት እቃዎችን፣ የደንብ ልብሶችን፣ የህከምና እቃዎችን፣ ሪኤጀንቶች መድሃኒቶች፣ የቢሮ ቋሚና ኤሌከትሪክ ዕቃዎችን ግዥ እና የተለያዩ ኤሌከትሮኒከስ የጥገና ስራ ከነማቴሪያል እንዲሁም ህትመትና መፅሐፍቶችን፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡

በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2018ዓ/ም

በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ በ2018ዓ/ም የስራ ዘመን የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን፣ አላቂ የፅዳት እቃዎችን፣ የደንብ ልብሶችን፣ የህከምና እቃዎችን፣ ሪኤጀንቶች መድሃኒቶች፣ የቢሮ ቋሚና ኤሌከትሪክ ዕቃዎችን ግዥ እና የተለያዩ ኤሌከትሮኒከስ የጥገና ስራ ከነማቴሪያል እንዲሁም ህትመትና መፅሐፍቶችን፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ለእያንዳንዱ ማስያዝ የሚገባቸው የጨረታ ማስከበሪያ

1. ሎት 1 አላቂ የፅህፈት መሳሪያ 9,000

2. ሎት 2 አላቂ የፅዳት እቃዎች 10,000

3. ሎት 3 የደንብ ልብስ ግዥና ስፌት 9,000

4. ሎት 4 የህክምና እቃዎች መድሃኒቶች ሪኤጀንቶች 30,000

5. ሎት 5 ቋሚ የቢሮና ኤሌከትሮኒስ እቃ ግዥና ጥገና የተለያዩ የጥገና እቃዎች 14,000

6. ሎት 6 የተለያዩ ህትመትና የህከምና መጻሕፍቶች 8,700

7. ሎት 7 የተለያዩ የጥገና ማስፋፊያ ስራ ማቴሪያል አቅርቦት 10,000

ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፤

1. በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት ተመዝግቦ በፌዴራል ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ኤጀንሲ የምስክር ወረቀት ያለው፡፡

2. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉና ንግድ ስም ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

3. ለተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) ተመዝጋቢ ለመሆናቸውና የግብር ከፋይ ቲንና የምዝገባ ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለባቸው፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ በአንድ ሎት 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) የህከምና እቃና የመድሃኒት ሎት 350 ብር (ሶስት መቶ ሃምሳ ብር) በመከፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ኮ/ቀ/ከ/ከተማ ወረዳ 3 ጤናጣቢያ ግራር ወፍጮ ወደ ሀናን ዳቦ ቤት መውጫ መንገድ ላይወረዳ 3 ጤና ጣቢያ 4 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 47 ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት እስከ ከቀኑ 11፡00 (አስራ አንድ ሰዓት ድረስ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው ቢሮ ቁጥር በመምጣት መግዛት ይቻላል፡፡

5. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ናሙና ወይም ሳምፕል ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ናሙናና ሳምፕል ለማቅረብ የማይመቹ ቋሚ እቃዎችን በፎቶግራፍ በስዕል በካታሎግ አጉልቶ በሚያሳይ ነገር ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ሌላው ተንተርሶ መስጠት አይችልም፡፡

7. ገዥው በአካል የሚገዛውን እቃ አስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡

8. ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በኢንቨሎፕ በማሸግና ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ለእያንዳንዱ ዋጋ ከዚህ በላይ የቀረበውን ዝርዝር በማየት በባንከ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ እንዳለባቸውና ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ወይም ቢሮ ቁጥር 53 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ወይም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

9. አሸናፊው ከታወቀ በኋላ ለተሸናፊዎች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለሳል፡፡

10. አሸናፊ ተጫራቾች በሰነዱ ውስጥ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም ከ7ቀን በኋላ ቀርበው የውል ማስከበሪያ 10% (አስር ፐርሰንት) በባንከ በተመሰከረለት ሲፒኦ አሰርተው ውል መዋዋል አለባቸው፡፡

11. ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡00 ሰዓት ታሸጎ በእለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ቢሮ ቁጥር 54 አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡

12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ በተለምዶ ግራር ኮንዶሚኒም ቤቶች አለፍ ብሎ ሀናን ዳቦ ቤት መውጫ መንገድ ላይ ይገኛል፡፡

ለበለጠ መረጃ-

ስልክ ቁጥር፡ 0920809099/0910268909 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 3 ጤና ጣቢያ

Save Tender