Tender Detail

Tender Details

  • Company በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ዳሌ ወረዳ /ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
  • Address በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ዳሴ ወረዳ ፣ ሲዳማ:ኢትዮጲያ, Phone: 0945853587
  • Website
  • Deadline08 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security2%
  • opening date2025-09-08 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial , Stationery Materials

በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ዳሌ ወረዳ /ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም ለሴ/ መ/ቤቶች የሚሆን የቢሮ የጽህፈት መሳሪያዎችንና የጽዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ዳሌ ወረዳ /ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ዳሌ ወረዳ /ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም ለሴ/ መ/ቤቶች የሚሆን የቢሮ የጽህፈት መሳሪያዎችንና የጽዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ተጫራቾች ሟሟላት ያለባቸው:-

1 ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የዕቃዎች አቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡

3. ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፍቃዳቸውንና ተ.እ.ታ [ቫት/ የተመዘገቡበት ሠርተፈኬት በማቅረብ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይቀናት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100 ብር በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ይርጋ-ዓለም ከተማ በሚገኘው ከዳሌ ወረዳ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 መግዛት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋ ብር 2% በባንክ በተረጋገጠ /ሲ/ፒ/ኦ/ ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በሰም በታሸገ በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ በሁሉም ዶከመንት ላይ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 5፡00 ሰዓት በይርጋ-ዓለም ከተማ በዳሌ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሴክተር ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን በዳሌ ወረዳ ፋይናስና ኢኮኖሚ ልማት /ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ከቀኑ 5፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

7. ጨረታ የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታ የሚከፈት ይሆናል፡፡

8. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ አንድ አንድ ትክከለኛ ናሙና ማቅረብ አለበት፡፡

9. የጨረታ አሸናፊ ያሸነፈው ዕቃ በእራሱ ወጪ ዳሌ ወረዳ /ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ማቅረብ አለበት፡፡

10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ፡- በስልከ ቁጥር 0945853587/ 0916370899/ 0967218758

 

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ዳሴ ወረዳ /ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

Save Tender