Tender Detail

Tender Details

  • Company የአጋዝያን ቁ.3 2ኛ ደ/ት/ቤት
  • Address Addis Ababa:Ethiopia, Phone: 0111110123
  • Website
  • Deadline08 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Security10,000.00
  • opening date2025-09-08 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial , Electronics Materials , Cloth And Shoes

የአጋዝያን ቁ.3 2ኛ ደ/ት/ቤት በ2018ዓ/ም በጀት ዓመት የሚከተሉት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የአጋዝያን ቁ.3 2ኛ ደ/ት/ቤት


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 01/2018ዐዓ.ም

የአጋዝያን ቁ.3 2ኛ ደ/ት/ቤት በ2018ዓ/ም በጀት ዓመት የሚከተሉት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

1- አላቂ የት/ት እቃዎችን፣ አላቂ የጽዳት እቃዎችን፣ የደንብ ልብስ፣የቢሮ እቃዎች፣ የፎቶ ኮፒ ቀለሞች፣ የስፖርት እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  • በዚህም መሰረት በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
  • ከተሰማሩበት የስራ መስከ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡እንዲሁም የንግድ መለያ ቁጥር Tin nummer) ማቅረብ ይኖርባዋል፡፡
  • በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ የንግድ ምዝገባ ማስረጃ ያለቸውና ባቅራቢነት ዝርዝርውስጥ የተመዘገቡ።
  • የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  • በመንግስት ጨረታ ላይ የመሳተፍ ጊዜ ያላለፈበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያገለግሉ የሚመረቱበትን የእቃ ዋጋውን ብር10,000.00/አስር ሺ ብር/ በጽሕፈት ቤቱ ስም የተዘጋጀ (ሲፒኦ) ወይም ጽሕፈት ቤቱ ፋይናንስ በካሽ በማስያዝ ማረጋገጡን ከመወዳደሪያው ሰነዶቻቸው ጋርማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ማንኛውም ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ናሙና ጨረታ ከመዘጋቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  • በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  • የምታስገቧቸው ሰነዶች ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሊኖረው አይገባም፣ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ውድቅ ነው የሚሆነው።
  • የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡበትን የጨረታ ሰነድ ከታሸገ ኤንቨሎፕ ኤጅናልና ኮፒ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  • ከሚሸጠው የጨረታ ስነድ ላይ የሚገለፅ የእቃ ብዛት የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው የሚሰሩ ነጋዴዎች የድጋፍ ደብዳቤ ስታመጡ ደብዳቤው በጽ/ቤቱ ኃላፊ ቲተርና ፊርማ ተፈርሞ ማምጣት ግዴታ ነው

ከላይ የተጠቀሱት እቃዎች ዝርዝር የሚያሳውቅና የግዥ መመሪያ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር በመከፈል ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፋ/ግ/ን/አ/ጽ/ቤት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

  • ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር የተጻፈ ሰነድ አጋዝያን ቁ.3 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጋዜጣው በወጣበት በክኛው (በአስራ አንደኛው) የስራ ቀን ጨረታው በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ላይ ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአጋዝያን ቁ3 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 1 ይከፈታል፡፡

 

መሥሪያ ቤቱ የተሻለ የግዥ ዘዴ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው መሰረዝ ይችላል።

አድራሻ፦ ጎጃም በረንዳ (ሀግቤስ) አቢሲኒያ ባንክ አጠገብ

ስተጨማሪ ማብራሪያ፡-

በስልክ ቁጥር 0111-11-01-23 /0111-11-42-10

ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በአራዳ ክፍስ ከተማ ት/ጽ/ቤት የአጋዝያን ቁ.3 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት

Save Tender