የባሌ ዞን ዲንሾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ላሉ ሴከተር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ ቶነሮች፤ ቋሚና አላቂ ዕቃዎች፣ የዕዳት እቃዎች፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች፣ ፈርኒቸሮች የግንባታ እቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች፣ የሠራተኞች ደንብ ልብሶች እና የልብስ ስፌት አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የባሌ ዞን ዲንሾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የባሌ ዞን ዲንሾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ላሉ ሴከተር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ ቶነሮች፤ ቋሚና አላቂ ዕቃዎች፣ የዕዳት እቃዎች፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች፣ ፈርኒቸሮች የግንባታ እቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች፣ የሠራተኞች ደንብ ልብሶች እና የልብስ ስፌት አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ ቀጥሎ የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች እንዲወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በ15/12 /2017 ዓመት በቁጥር በወጣው ግልጽ ጨረታ መሠረት ከዚህ በታች የተገለፁትን መመሪያዎች በመከተል ተጫራቾች መጫረት ይችላሉ:፦
1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል የሚያስችል በሚወዳደሩበት ዘርፍ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር ከፍለው ያሳደሱና በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸል፡፡
2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል::
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 20,000.00 (ሃያ ሺህ) ብር የያዘ በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን ሰነዶች ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ፋይነንሽያል ኦርጅናል እና ኮፒ፣ በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5 አቅራቢው ድርጅት ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀለት ከ5ኛው ቀን በኋላ ከ6ኛው ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ መ/ቤቱ ቀርቦ ውል መፈራረም ይኖርበታል፡፡
6. የደንብ ልብስ ናሙናዎችን ጨረታ ሰነድ ላይ የወጡትን በሙሉ ጨረታው ከመከፈቱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ማቅረብ አለበት፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይየሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 / ሦስት መቶ/ ብር በባሌ ዞን ዲንሾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000115558009 በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ በማስገባት ሰነዱን ከቢሮ ቁጥር 1 መውሰድ ይችላሉ፡፡
8. ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
9. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0912254856/0912706097 ደውለው ይጠይቁ፡፡
በባሌ ዞን የዲንሾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
