በኮልፌ ቀራንዮ ከፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጋራፉሪየመ/ደ/ት/ቤት የ2018 በጀት ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ጋራፉሪየመ/ደ/ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኮልፌ ቀራንዮ ከፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጋራፉሪየመ/ደ/ት/ቤት የ2018 በጀት ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1፡- የፅህፈት መስሪያ እቃዎችና ሌሎች
ሎት 4፡- የላብራቶሪ እቃዎች የትምህርት መርጃ መሳሪያና እና መፅሐፍት
ሎት 2፡- የፅዳት እቃዎች
ሎት 5 የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸሮች እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
ሎት 3፡- የደንብ ልብሶች
ሎት6፡- የተለያዩ ህትመቶች
ሎት7፡- ለፕላንት ማሽነሪ እና ለመሳሪያ ዕድሳትእና ጥገና፡ለህንፃ ቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚ ዕድሳት እና ጥገና ለመሰረተ ልማት ዕድሳት እና ጥገና፡፡
1.ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሰነድ ማስረጃዎችን ዋናውንና ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
2.ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
3.ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር በፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የተመዘገበ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
4.ተጫራቾች የተዘረዘሩትን እቃዎች ናሙና ማቅረብ የሚችሉና ቋሚ እቃዎች በፎቶ እና ገዥው መ/ቤት ድርጅታችሁ በአካል መጥቶ ለማየት ከፈለገ ለመተባበር ፊቃደኛ ሊሆኑ የሚችሉ 1 መሆን አለበት፡
5.ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ 1 ጀሞ2 ሸገር ማዞሪያ 200 ሜትር ገባ ብሎ አማኑኤል ቤተክርስቲያን አከባቢ ከሚገኘው የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የጋራፉሪ የመ/ደ/ት/ቤት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር ብቻ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
6.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ( ሎት1 )13,620 አስራ ሶስት ሺህ ስድስት መቶ ሃያ ብር(ሎት2 )10,455 አስር ሺህ አራት መቶ ሀምሳ አምስት ብር (ሎት3 )10,664 አስርሺህ ስድስት መቶ ስልሳ አራት ብር (ሎት4) 1500 አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር (ሎት5) 50,000 ሀምሳ ሺህ ብር (ሎት6)1000 አንድ ሺህ ብር ሎት7)40,000 አርባ ሺህ ብርሲሆን በተረጋገጠ ሲፒኦ በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የጋራ ፉሪ የመ/ደ/ት/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ በት/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ ቀን 2፡30 እስከ ቀኑ10፡30 በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ሰነድ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡00ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
7. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት እቃዎች በሙሉ ጨረታ ከመከፈቱ 1ቀን በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸወ፡፡
8 ተጫራቾች በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ መሙያ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ በግልፅ መሙላት አለባቸው፡
9.ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ /cpo/ በተረጋገጠ ቼክ በመስሪያ ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
10. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረበበት ዋጋ ላይ የዋጋ ለውጥም ሆነ ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡ በተወዳደሩበት ዋጋ አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ በ 7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቀርበው የውል ማስከበሪያ 10% ለግዢ ፈፃሚ አካል ማስያዝ አለባቸው፡ያስያዙትን ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው በውሉ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ከታወጡና ውሉ ተመላሽ ሲደርጉ ነው፡፡
11. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. እቃውን የሚያስገቡበት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ሲሆን ከ ሰዓት 7፡00 እስከ 9፡00 ሰዓት ድረስ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ከተጠቀሰው ሰዓት ውጪ የሚመጡ ከሆነ የማናስተናግዳቸው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
አድራሻ፡ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጋራ ፉሪ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቱ ልዩ ቦታው ጀሞ2 ሸገር ማዞሪያ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ 200 ሜትር አማኑኤል ቤተክርስቲያን አጠገብ
ስልከ ቁጥር 09 21 59 19 36 /09 10 00 74 65
አበባ ከተማ አስተዳደር በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ
ወረዳ 02 ጋራ ፉሪ ቅ/አንደ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
