በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን የጭሮ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት በጭሮ ወረዳ ውስጥ ለሚገኙ ለተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለስራ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ እና ቋሚ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒከሶች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ላፕቶፖች፣ ለትምህርት መርጃ አገልግሎት የሚውሉ ጠመኔዎች እና ሌሎችንም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን የጭሮ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን የጭሮ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት በጭሮ ወረዳ ውስጥ ለሚገኙ ለተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለስራ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ እና ቋሚ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒከሶች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ላፕቶፖች፣ ለትምህርት መርጃ አገልግሎት የሚውሉ ጠመኔዎች እና ሌሎችንም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የታደሰና የዘመኑን (2017 ዓ.ም) ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ አቅራቢዎችም ከላይ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚጫረቱበትን የመወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ ከ VAT ጋራ በመጥቀስ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አድርገው እስከ መስከረም 07 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ በቢሮ ቁጥር 3 ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ ጨረታው በዚያኑ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች ወይም የሀጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት እያግደውም፡፡
4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ መስከረም 07 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ለተጫራቾች ክፍት ይሆናል፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል ከዚህ በላይ በተገለጸው ጽ/ቤት አድራሻ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በአካል በመቅረብ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በመላክ መግዛት ይችላሉ፡፡
6. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት አስከ ጭሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት እቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ አሸናፊው ድርጅት እቃዎቹን በተጠየቀው ብዛትና ጥራት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
7. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
8. የማስጫኛ እና የማውረጃ ወጪ በተጫራቹ ይሸፈናል፡፡
9. ለሽያጭ የቀረበው እቃ ጥራቱን ያልጠበቀ ከሆነ ድርጅቱ በራሱ ወጪ እቃውን የመለወጥ ወይም ገንዘቡን የመመለስ ግዴታ አለበት፡፡
10. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው::
11. ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
12. ተጫራቾች በሰነዱ ላይ ባሸነፉበት የእቃ ዓይነት ሙሉ በሙሉ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው::
13. መስሪያ ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ ሌላ ሰነድ በአማራጭነት ማቅረብ አይቻልም፡፡
14. ተጫራቾች ያሸነፉበትን 10% የውል ማስከበሪያ (Performance Bond) ለማስያዝ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው፡፡
15. ተጫራቾች በአቀራቢነት ዝርዝር (suppliers List) ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- አድራሻችን ምዕ/ሐ/ዞን ጭሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር፡- 09-11-95-03-43/ 025-5-51-13-14
ጭሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
