Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መ/በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
  • Address ከአዲስ አበባ ርቀቱ 221 ኪሎ ሜትር ቂልጦ ከተማ ስልጤ ዞን : ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 21 33 86 96
  • Website
  • Deadline09 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price150.00
  • Bid Security20,000 ብር
  • opening date2025-09-09 00:00:00
  • Categories 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በስሩ ላሉ መሥሪያ ቤቶች የሚውሉ ሞተር ሳይክሎች እና ገልባጭ ባጃጅ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መ/በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በስሩ ላሉ መሥሪያ ቤቶች የሚውሉ ሞተር ሳይክሎች እና ገልባጭ ባጃጅ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ፡- ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለ ዕቃዎቹ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 150 (አንድ መቶ ሃምሳ) ብር ብቻ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት በምስ/አዘ/በር ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በመምጣት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነድ መግዛት ትችላላችሁ፡፡

በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የቫት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ተጫራቾች ለጨረታው ማስረከቢያ /CPO/ 20,000 ብር ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፉትን እቃ ምስ/አዘ/በ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ገቢ ማድረግ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ የትራንስፖርት፣ የማስጫኛና የማውረጃ ጨምሮ በጨረታው ሰነድ ላይ በመሙላት ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. አንዱ ባቀረበው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  8. ጨረታው በ15ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል፡፡
  9. በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ ፋይናንሻል ዋጋዎች በግልጽና በጥራት የሚታዩና ስርዝ ወይም ድልዝ ያልሆኑ መሆን አለባቸው።
  10. ተጫራቾች በሚፈልጉት ዕቃ ላይ መወዳደር ይችላሉ ሆኖም ለአንድ ዕቃ ከተጠየቀው ብዛት አሳንሶ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  11. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. ወረዳው ከአዲስ አበባ ርቀቱ 221 ኪሎ ሜትር ሲሆን 176 ኪሎ ሜትር አስፓልት እና 45 ኪሎ ሜትር ፒስታ መንገድ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 21 33 86 96/09 33 62 02 20

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መ/በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት

ቂልጦ

 

Save Tender