Tender Detail

Tender Details

  • Company አንበሣ ጫማ አ.ማ
  • Address Addis Ababa:Ethiopia, Phone: ----------
  • Websitehttps://www.addismap.com/am/p-252678/anbessa-shoe
  • Deadline01 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security5,000.00
  • opening date2025-09-01 00:00:00
  • Categories Vehicle

አንበሣ ጫማ አ.ማ አቃቂ ቃሊቲ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

አንበሣ ጫማ አ.ማ


ያገስገሱ ተሽከርካሪዎች የጨረታ ማስታወቂያ

አንበሣ ጫማ አ.ማ አቃቂ ቃሊቲ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች አቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 2 በሚገኘው ዋናው መ/ቤት በመገኘት ተሽከርካሪዎችን ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡

2. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል አቃቂ ከሚገኘው ፋብሪካ የፋይናንስ ዋና ከፍል መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በካሽ ከሆነ አቃቂ ፋብሪካ በሚገኘው የድርጅቱ ፋይናንስ ዋና ክፍል በመከፈል ደረሰኙን ወይንም ሲፒኦ በማሰራት የምትገቡትን ዋጋ በግልጽ በመጥቀስ የክፍያ ደረሰኙን ሰነድ አያይዛችሁ በዋናው ፋብሪካ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን በማስገባት መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

4. ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ከቫት በፊትና በኋላ በሚል በግልጽ መጥቀስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ሌላ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡

5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ10 ቀን በኋላ ባለው የስራ ቀን ላይ በ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ወዲያውኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ መሆናቸው በተገለፀላቸው በ 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ተሽከርካሪ ሙሉ በሙሉ ማንሳት ይጠበቅባቸዋል፡ ፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካላነሱ ግን ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ በድጋሚ ጨረታ በማውጣት እንዲሸጥ ይደረጋል፡፡ “አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አንበሣ ጫማ አ.ማ

Save Tender