Tender Detail

Tender Details

  • Deadline04 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security2%
  • opening date2025-09-04 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial

በደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ የመካነ-ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል የጽዳት ስራን አውት ሶርስ በማድረግ ለአንድ አመት ቆይታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማፀዳት ይፈልጋል፡፡


 

ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ የመካነ-ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል የጽዳት ስራን አውት ሶርስ በማድረግ ለአንድ አመት ቆይታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማፀዳት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች በዝርዝር የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟላ መወዳደር ይችላል፡፡

  1. በመ/ሰ/ጠ/ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ የሚገኘውን እና አሁን በክልሉ በኩል እየተገነባ ያለው የማስፋፊያ ግንባታ የአገልግሎት መስጫ ክፍሎችና የቅጥር ግቢውን ንፅህና የሚጠብቅና የሚያፀዳ፡፡
  2. በጥቃቅን አነስተኛ ህግ በሚያዘው መሰረት የተደራጀና መረጃ ማቅረብ የሚችል በመመሪያው መሰረት ይፈጸማል፡፡
  3. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለውና በዘመኑ የታደሰ መሆኑን የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. ሆስፒታሉ በሚፈልገው መሰረት የተመረጠውን ከለርና ስፌት የደንብ ልብስ በስራ ሰአት በራሱ ወጭ አሟልቶ መልበስ የሚችል፡፡
  5. ጨረታው የሚከናወነው በሎት ነው።
  6. ማንኛውም የጽዳት ዕቃዎች ለምሳሌ፡- በረኪና፣ ኦሞ፣ ላርጎ፣ ቪም፤ ድቶል የፕላስቲክ መጥረጊያ፣ መወልወያ እና ባልድና ፎጣ በራሱ ወጭ አሟልቶ ማጽዳት የሚችል፡፡
  7. በጽዳት ስራ ላይ የሠራተኞች ብዛት 12 የሚሆንና ቅዳሜ፣ እሁድ፣ የህዝብ በአላት እና የአዘቦት ቀን በ24 ሰዓት ውስጥ በጽዳት ስራ ላይ መገኘት አለባቸው።
  8. የመጸዳጃ ቤቶች ንጽህና በመጠበቅ የሽንት ቤት መርዝ በመጠቀም መፀዳጃ ቤቶች ሽታ አልባ መደረግ አለባቸው።
  9. የበረኪና አንድ ለዘጠኝ ውህደትን በመጠቀም የአገልግሎት መስጫ ከፍሎችን በመወልወል ንፅህናቸውን የሚጠብቅ፡፡
  10. አሸናፈው ተጫራች (ማህበሩ) በጽዳት ወቅት በየአገልግሎት መስጫ ክፍሎች የሚገኙትን ንብረቶች የጽዳት ሠራተኛው በእንዝላልነትና በግደለሽነት ምክንያት ለጠፋ/ለሚጠፋ ሠነዶች ቋሚና አላቂ እቃዎች የመንግስት ሀብትና ንብረት የሚከፍልና በህግ የመጠየቅ ግደታ አለበት፡፡
  11. በሆስፒታሉ ህግና ደንብ መሰረት ተገዥ የሆነና ሌሎች ከጽዳት ጋር የተያያዙ ስራዎችንና የሚሰጠውን ማንኛውንም ተግባር ተቀብሎ መፈፀም የሚችል፡፡
  12. ማሀበሩ መድቦ በሚያሰራው የጽዳት ሠራኞች የሚፈጠር ማንኛውንም ችግር ማህበሩ በህግ ተጠያቂ ይሆናል፡፡
  13. በወር ለአገልግሎትና ለጽዳት እቃዎች ግዥ መጠየቂያ ደመወዝን ጨምሮ ሊከፍለው የሚችለውን ገንዘብ መጠን በኢትዮጵያ ብር ጥቅል ድምር በተዘጋጀው የመወዳደሪያ ሰነድ በወር እና በአመት የሚለው ጨረታ ሰነድ ላይ በትክክል መሙላት አለበት፡፡
  14. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከመ/ሠ/ጠ/ሆ/ ዋና ገንዘብ ያዥ መግዛት ይችላሉ፡፡
  15. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ሰነዱ ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ በሞደል 85 ማሲያዝ አለባቸው፡፡
  16. በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም በተጨማሪም በተለያዩ እስኪርብቶ ጽፎ ማቅረብ የለበትም።
  17. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ዋጋ በተዘጋጀው ሠነድ ላይ በመሙላት በደንብ በታሸገ ፖስታ መካነ-ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል ዘወትር በስራ ስዓት ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ዘወትር ተከታታይ 16 የስራ ቀናት በአየር ላይ ይውላል የጨረታ ሰነዱ ዘወትር በስራ ስአት ከግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይዘጋል ቅዳሜ እና እሁድ (በአል) ላይ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  18. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ከሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  19. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ /በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  20. ጨረታውን መሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው መረጃ ከፈለጉ ከግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09-34-37-02-54/ 09-14-34-43-06 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

 

የመካነ-ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል

 

Save Tender