የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮው የሚያስፈልጉ የተለያዩ እቃዎች አገልግሎቶች ሎት 1፡- የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2:- ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሎት 3፡- የኤቨንት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Addis Ababa City Administration Industry Development Bureau (አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ)
የጨረታ ማስታወቂያ 001/2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮው የሚያስፈልጉ የተለያዩ እቃዎች አገልግሎቶች ሎት 1፡- የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2:- ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሎት 3፡- የኤቨንት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች:-
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው። በኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡበት ማስረጃ ማያያዝ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፒያሳ የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ህንፃ (ዋስትና የንግድ ማዕከል 18ኛ ፎቅ ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ህጋዊ ሥልጣን ያለው አካል ፊርማና ማህተም በማኖር በሰም በታሸገ ማህተም ያረፈበት ኤንቨሎኘ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፒያሳ የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ህንፃ (ዋስትና የንግድ ማዕከል) 18ኛ ፎቅ የግዥ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11ኛው ቀን በዓል ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረለት ቼከ ወይም CPO ማስያዝ አለባቸው። እያንዳንዱ ተወዳዳሪ የቴክኒክና የፋይናንስ ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
- በሌሎች ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑበትን እቃዎች አገልግሎቶች በወቅቱ በተገቢው የማስረከብ እና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- ሎት 1 እና ሎት 2 የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን አገልግሎቶች በውላቸው መሠረት በወቅቱ በሚሰጡ ትዕዛዞች መሰረት ማቅረብ አለባቸው ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ7 ቀን ውስጥ ቀርበው ውል መዋዋል አለባቸው።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0111262185
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ
