የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል ጨረታ ቁጥር (1) በእንጨትና ብረታ ብረት ለትምህርትና ስልጠና ስራዎች አገልግሎት የሚውል የጥሬ ዕቃ ግብዓቶች፤ የጨረታ ቁጥር (2) የጥገና፤ የቧንቧ፣ የመሰረተ ልማት፤ የኤሌክትሪክና የግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፈው ድርጅት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል
የጨረታ ማስታወቂያ
የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል ጨረታ ቁጥር (1) በእንጨትና ብረታ ብረት ለትምህርትና ስልጠና ስራዎች አገልግሎት የሚውል የጥሬ ዕቃ ግብዓቶች፤ የጨረታ ቁጥር (2) የጥገና፤ የቧንቧ፣ የመሰረተ ልማት፤ የኤሌክትሪክና የግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፈው ድርጅት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት:-
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ፣ በሥራው መስክ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በዕቃ ግዢና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበት የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ እና መለያ ቁጥር (Tin Number) ተመዝጋቢ የሆኑና የተሟላ ማስረጃ በ4 ኮፒ በማድረግ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን አንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በእያንዳንዱ ሰነድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 100000797188 አ/አ ማረ/ቤት እደ-ጥበባት ማዕከል በሚል ገንዘቡን ገቢ በማድረግ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል ግዥ ክንውን ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ። ማረ/ቤቱ የሚገዛቸውን ዕቃዎች ዝርዝር በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ተዘርዝሮ ቀርቧል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ በጨረታ ቁጥር 1-2 ለተጠቀሱት ጨረታዎች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚመለስ ለእያንዳንዳቸው ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች አንዱ በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ናሙና እንዲያቀርብ የተጠየቀባቸው ናሙናውን በጨረታ መክፈቻ ቀን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሠነድ መግዛትና የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ቁጥር 1 ነሐሴ 28/2017 ዓ/ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዳቸውን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዕለቱ በ4፡15 ሰዓት በማረ/ቤቱ በግዥ ክንውን ቢሮ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ቁጥር 2 ነሐሴ 29/2017 ዓ/ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት ይችላሉ። በዕለቱ በ4፡15 ሰዓት በማረ/ቤቱ በግዥ ክንውን ቢሮ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት እንዳስፈላጊነቱ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል በሚገኘው ዕቃ ግ/ቤት በአንድ ጊዜ አምጥተው ያስረክባሉ።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- ማረሚያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ፕሮፎርማቸው ላይ ዋጋ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ የሌለበት ጎላ ብሎ የሚነበብ ፅሑፍ መሆን ይገባዋል፤ ስርዝ ድልዝ ያለበት ዋጋ ተቀባይነት የለውም። በአሃዝና በፊደል መፃፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡
አድራሻ፡- ገላን
ለበለጠ መረጃ- 011-4-39-76-61 ወይም 011-8-88-91-81
የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል
