በአብክመ የኦሮ ብ/ዞን የባቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ባሉ በአራቱም ፑሎች በሚገኙ ንብረት ክፍሎች ውስጥና ውጭ በግቢ ውስጥ የሚገኙ አሮጌ ብረታ ብረቶች፤ የተቀየሩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የባቲ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
ግልጽ የሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የግልፅ ጨረታ ቁጥር 001/2018
በአብክመ የኦሮ ብ/ዞን የባቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ባሉ በአራቱም ፑሎች በሚገኙ ንብረት ክፍሎች ውስጥና ውጭ በግቢ ውስጥ የሚገኙ አሮጌ ብረታ ብረቶች፤ የተቀየሩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶችን ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡30 የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ መዝጊያው ቀን ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደርበት የጨረታ አይነት ጠቅላላ ዋጋ ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በመ/ቤታችን ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና እና በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ አለባቸው።
- ሰነዱ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ከ10/12/2017 ጀምሮ እስከ 24/12/2017 ድረስ አየር ላይ ይውላል። በ25/12/2017 ከጠዋቱ 3፡30 ሳጥኑ ይታሸጋል። ጨረታው የሚከፈተው በተመሳሳይ ቀን ከጧቱ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይቀንና ሰዓት ይሆናል።
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
- ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ እቃ በድጋሚ ለሽያጭ የሚቀርብ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0335532123 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።
በአብክመ የኦሮ ብ/ዞን የባቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
