በሸገር ከተማ አስተዳደር የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለክ/ከተማው ሴክተር መ/ቤቶች የተለያዩ መጠን ያላቸውን የመኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በሸገር ከተማ አስተዳደር የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ ጨረታ
በሸገር ከተማ አስተዳደር የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለክ/ከተማው ሴክተር መ/ቤቶች የተለያዩ መጠን ያላቸውን የመኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ በመከተልና ከዚህ ጋር ተያይዞ በቀረበው እስፔስፊኬሽን መሰረት ተጫራቾች ይህንን ጨረታ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።
የጨረታ መመሪያ፡-
- ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ Tin ተመዝጋቢ የሆኑ፤ በአቅራቢዎች ዝርዘር የተመዘገቡና ግብር መክፈሉን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች ሰነዱን ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 21 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ብር በሲንቄ ባንክ አካውንት 1064628071215 በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ጨረታው በ21ኛዉ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ባለቤት ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን ይከፈታል። እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግድም፡፡
- ተጫራቾች ሙሉ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ በ10 (አስር) ቀን ውስጥ ውል መፈጸም አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታ ሂደት ውስጥ ቅሬታ ካለው የጨረታው ውጤት ተገልጾ ከ5 (አምስት) ቀን በኋላ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ለሁሉም አቃዎች ቫትን (VAT) ጨምሮ መሙላት እና አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉበትን የእቃ አይነቶች እስከ መስሪያ ቤታችን ግምጃ ቤት ድረስ ማድረስ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ የመቆያ ጊዜ (price Validity date) ከጨረታው መክፈቻ እለት ጀምሮ የሚጸናበትን ጊዜና ስራውን አጠናቆ የሚያስረክብበትን ጊዜ (delivery time) መግለጽ ይኖርባቸዋል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት መረዳት ይችላሉ፡፡
የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
