Tender Detail

Tender Details

  • Company የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
  • Address ደብረ ብርሃን : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116375610
  • Website
  • Deadline31 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityየተሽከርካሪዎች ጥገና ሰርቪስ 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/፣ ለተሽከርካሪ ኢንሹራንስና ዋስትና አገልግሎት ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) እና የእንስሳት መድሀኒትና የህክምና መሳሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
  • opening date2025-08-31 00:00:00
  • Categories Veterinary Equipment And Supplies , Insurance Service , Vehicle (Garage Service)

የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለ2018 በጀት ዓመት የተሽከርካሪ ጥገናና ሰርቪስ አገልግሎት፣ የተሽከርካሪ ኢንሹራንስ ዋስትና አገልግሎትና የእንስሳት መድሀኒትና የህክምና መሳሪያ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡

የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ


 

ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለ2018 በጀት ዓመት የተሽከርካሪ ጥገናና ሰርቪስ አገልግሎት፣ የተሽከርካሪ ኢንሹራንስ ዋስትና አገልግሎትና የእንስሳት መድሀኒትና የህክምና መሳሪያ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ ብር) በላይ በመሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. በተሽከርካሪ ጥገናና ሰርቪስ በዘርፉ የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ያለው ሆኖ ደረጃ 2 ወይም ደረጃ 3 እና በላይ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰርተፊኬት ያላቸው፣
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብና በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የተሽከርካሪዎች ጥገና ሰርቪስ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በጨረታ ሠነዱ የተገለፀውን የብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/፣ ለተሽከርካሪ ኢንሹራንስና ዋስትና አገልግሎት ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) እና የእንስሳት መድሀኒትና የህክምና መሳሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንከ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ስም በመክፈል የተከፈለበትን ደረሰኝ ከሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሃሳባቸውን /ሰነዳቸውን/ ደብረብርሃን ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በሚቆጠር ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደ/ብ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት አንስቶ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ 4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
  10. በጨረታው የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች የተሽከርካሪ የጥገናና ሰርቪስ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል በደብረብርሃን ከተማ የጥገና ተቋም ያላቸዉ እና የተሽከርካሪ ኢንሹራንስ ዋስትና በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች በኢንሹራንስ ዋስትና በደብረብርሃን የአገልግሎት መስጫ ቅርንጫፍ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ግዥ ፈጻሚ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 011-637-56-10 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

 

የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ (ደብረ ብርሃን)

 

Save Tender