አይናጌ የሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት ለ2017/18 ዓ.ም በጀት ዓመት ለተማሪዎች በጠቅላላው 16,750 (አስራ ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ) ሲነር ላየን ባለ 50 ሉክ ልሙጥ ደብተር የተለበደ አንደኛ ደረጃ ደብተር መግዛት ይፈልጋል፡፡
አይናጌ ሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት
በድጋሚ የወጣ የተማሪ ደብተር ግዢ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ስልጤ ዞን በቅበት ከተማ አስተዳደር የሆነው አይናጌ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት በመዝገብ ቁጥር 1544 ዳግም ተመዝግቦ ሕጋዊ ፍቃድ ያለው ድርጅት ነው።
ድርጅቱ ለ2017/18 ዓ.ም በጀት ዓመት ለተማሪዎች በጠቅላላው 16,750 (አስራ ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ) ሲነር ላየን ባለ 50 ሉክ ልሙጥ ደብተር የተለበደ አንደኛ ደረጃ ደብተር መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ በዘርፉ የተሰማራ ማንኛውም ድርጅት የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የቫትና የተርን ኦቨር ሰርተፍኬት ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ስራዎችን ሰርቶ የመልካም አፈጻጸም ደብዳቤ ካለና ሌሎች ለጨረታው አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችንና በማይመለስ ብር 700 (ሰባት መቶ ብር ብቻ) የዋጋ ማቅረቢያ ደብዳቤ (ሰነድ) ገዝቶ በመሙላት እንዲሁም የሚወዳደርበትን ጠቅላላ ዋጋ ቢያንስ 2 ፐርሰንት CPO በባንክ በተረጋገጠ ጨምሮ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ድርጅቱ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ማስገባት የሚችል መሆኑን እየገለፅን ጨረታው በ10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ 8:30 ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡ ተጫራቹ ደብተሮችን በራሱ ትራንስፖርት ድርጅቱ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል ።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡- 0468820140/0468800440
አይናጌ የሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት
