የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ሚ/አ/ከ/ዋና ማዘጋጃ ቤት በባለቤትነት ለሚያሰራው ለመንገድ ጥገና ስራ አገ/ት የሚውል፡- ሎት 1፡- የዶዘር ማሽን ሎት 2፡- የኤከስካቫተር ማሽን ኪራይ በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ሚ/አ/ከ/ዋና ማዘጋጃ ቤት በባለቤትነት ለሚያሰራው ለመንገድ ጥገና ስራ አገ/ት የሚውል፡-
- ሎት 1፡- የዶዘር ማሽን
- ሎት 2፡- የኤከስካቫተር ማሽን ኪራይ በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት
1. ተጫራቾች በማሸነሪ ኪራይ የሥራ መስከ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
3. በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
5. ግብር ስለመከፈላቸው ከገቢዎች መ/ቤት ከሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
6. የጨረታ ሰነድ ከግዥ ኬዝ ቲም የሥራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን ብር /5ዐዐ/ አምስት መቶ ብር ከፍለው በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ።
7. የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ሲመልሱ ቴክኒካሉን 1 ኦሪጅናልና 2 ኮፒ ፋይናንሻሉን 1 ኦሪጅናልና 2 ኮፒ በሁለት ፖስታ በማድረግ እና በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ 400,000 /አራት መቶ ሺህ ብር/ ለሎት ሁለት 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ከታወቀ ባንከ የሚሰጥ የተረጋገጠ ቼከ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና እና በባንከ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ከሬዲት ለሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በማለት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ29 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ30ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሁለቱም ታሽጎ በዚያው ቀን ሎት አንድ በ4፡00 ሰዓት ላይ ሎት ሁለት 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
10. ሰነዱን ሞልተው ወደ ጨረታ ሳጥን ለማስገባት ሲመጡ ተመዝግበውና ፈርመው ማስገባት አለባቸው።
11. በጨረታው ማስታወቂያ ላይ የትርጉም ስህተት ቢኖር በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፀው ተቀባይነ ይኖረዋል።
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
