Tender Detail

Tender Details

  • Company ኮምቦልቻ ምስራቅ አማራ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት
  • Address ኮምቦልቻ ምስራቅ አማራ፣ኢትዮጲያ, Phone: 0335510230
  • Website
  • Deadline12 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityለየሎቱ የተለያየ
  • opening date2025-09-12 00:00:00
  • Categories Vehicles Rent

የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ተሽከርካሪዎች ኪራይ ግልፅ ጨረታ

ኮምቦልቻ ምስራቅ አማራ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት


የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ተሽከርካሪዎች ኪራይ ግልፅ ጨረታ ቁጥር

WWC/ma. & veh/re/01/2018 የጨረታ መመሪያ

1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑ ግብር የከፈሉበት ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ስራ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እና በጨረታው  ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ተጫራቾች የንብረቱ ባለቤት ስለመሆኑ ወይም ህጋዊ ውክልና ያለው /በውክልናው ምን አይነት ኃላፊነቶችን እንዲያስፈጽም የተወከለ ስለመሆኑ/ በግልጽ የሚያስረዳ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል።

2- የጨረታ አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ነው፡፡

3- በዚህ ጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ 20 /ሃያ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ በመምጣት የማይመለስ ብር200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ የውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ሂሳብ ቁጥር 1000265163223 ገቢ በማድረግ እና የባንክ ስሊፕ በማቅረብ ወይም በቀጥታ ከኮርፖሬሽናችን የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ ሰነዱ የሚሸጥባቸው ቦታዎች ባህርዳር ዋናው ቢሮ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 25 ፥ በአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት እና ኮምቦልቻ

ምስራቅ አማራ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 ነው::

4- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመሣሪያ ብዛት መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ቀላል ተሽከርካሪ /አምቡላንስ ዳብል ጋቢና፣ ሲንግል ጋቢና፣ ሚኒ ጋቢና፣ ሚኒ ባስ አውቶሞቢል፣ ስቴሽን ዋግንና ተመሳሳይ ለሆኑት /10 ሺህ ብር/ መለስተኛ የህዝብና የጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች አይሱዙና አውቶብስ/ 15ሺህ ብር፣ ከባድ ተሽከርካሪ /ገልባጭ 120 ኩንታል በላይ የሚጭኑ የደረቅ እና የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ፣ ሚክሰር፣ ትራክተር፣ ክሬን/ 20 ሽህ ብር፣ ለቀላል ማሽነሪዎች/ኮምፖከተር፣ ሎደር/ 25 ሽህ ብር እና ለከባድ ማሽነሪነዎች /ዶዘር ፣ ኤክስካቫተር ፣ ግሬደር ፥ ሎቤድ/ 30 ሽህ ብር CPO ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል /Unconditional Bank guarantee/ የባንከ ጋራንቲ በማሰራት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ከዚህ ውጭ  በ ሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡

5- ተጫራቾች የማወዳደሪያ ሠነዳቸው በታሸገ ፓስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂዯ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምር ባሉት ተከታታይ 20 ቀናት ወስጥ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤታችን ውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽ ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 25 በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

6- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 አዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ህንጻ 3ኛ ፎቅ የግዥ አፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 25 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች  በራሳቸው ፈቃድ ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት አያስተጓጎልም:: ከዚህ በተጨማሪ በ በጨረታ ሂደቱ ለሚተላለፉ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡ የጨረታው መከፈቻ እና መዝጊያ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚቀጥለው የሥራ ቀን  በተመሳሳይ ሰዓት  ተዘግቶ ይከፈታል፡፡

 

7-ተጫራቾች በጨረታው መመሪያ መሠረት የመጫረቻ ሰነዳቸውን  ማቅረብ አለባቸው

ከጨረታው መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነ የለውም፡ ::

8 ተጯራቶች በአንድ ማሽን ወይም ተሽከርካሪ መወዳደር የሚችሉት እንድ ኘሮጀከት ብቻ ላይ ነው፡፡

9- ኮርፖሬሽን የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል  የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

10- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡

 

የስልክ ቁጥር ባህር ዳር 058-222-1479 ወይም 058-226-5203

አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት 011-443-2595

ኮምቦልቻ ምስራቅ አማራ ኮንስትራክሽን  ጽ/ቤት

033-551-0230 033-5510848

የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን

 

Save Tender