የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ሙሉ የመድን ካሣ ከፍሎ ያስቀራቸውን ጋቢናዎች በተናጥል በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ሙሉ የመድን ካሣ ከፍሎ ያስቀራቸውን ጋቢናዎች በተናጥል በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ጋቢናዎቹን ቃሊቲ ክራውን ሆቴል በስተጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል በመገኘት ከነሐሴ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በመመልከትና የጨረታ ማስከበሪያ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት (ETHIOPIAN INSURANCE CORPORATION) ስም ሲ.ፒ.ኦ. በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
የማስያዣ ዋጋው የጨረታ መነሻውን 20 በመቶ ሲሆን ዝቅተኛ የጋቢና የማስያዣ ዋጋ ብር 1000 ነው።
ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት በመሙላት የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ነሐሴ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ቃሊቲ በሚገኘው በማዕከሉ ግቢ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ጨረታው ነሐሴ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቃሊቲ በሚገኘው በሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል ይከፈታል። በጨረታው ተሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ከሁለት የሥራ ቀናት በኋላ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን፣ ለአሸናፊዎች ግን ሂሳቡ በገዙት ንብረት ላይ የሚታሰብ ሆኖ የገዙት ንብረት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የገዙበትን ዋጋ አጠናቀው በ10 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ባይረከቡ ለጨረታ ተሳትፎ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ መልክ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል። ክፍያ ፈፅመው ንብረቶቹን በተገለፀው ጊዜ የማያነሱ ተጫራጮች የጥበቃ ወጪ በቀን ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ይከፍላሉ።
የጨረታው አሸናፊ በተቀመጠው ቀን ገደብ ውስጥ ከከፈለ በኋላ ንብረቱን በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ካላነሳ ከክፍያው ላይ የቅጣት ተቀንሶ ቀሪ ሂሳብ ካለው ተመላሽ ይደረግለታል።
ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ያሸነፈውን ጋቢና በአለበት ሁኔታ በአንድ ጊዜ ማንሳት አለበት። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 011439-25-89 እና 011439-25-45 መጠየቅ ይቻላል።
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት
