የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አጠቃላይ የፅዳት ኬሚካሎች እና ግሊሲሪን በቋሚነት ሊያቀርቡ የሚችሉ አምራች ድርጅቶችን ብቻ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ -SSNT-T560
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አጠቃላይ የፅዳት ኬሚካሎች እና ግሊሲሪን በቋሚነት ሊያቀርቡ የሚችሉ አምራች ድርጅቶችን ብቻ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል። ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ በዘርፉ (ፈሳሽ እና ወይም ደረቅ የገላ ሳሙና ዱቄት ሳሙና/በረኪና / ግሊሲሪን) በማምረት ሁለት (2) ዓመት እና ከዛ በላይ የሰሩ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በዘርፉ ከኢትዮጵያ የጥራትና ደረጃዎች ማረጋገጫ ባለስልጣን የጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ ከኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የተሰጠ የአምራችነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ፣ የተፈላጊውን ምርት ናሙና ማቅረብ የሚችሉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ውስጥ ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር (አንድ መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T560 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ በ5:40 ሰዓት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ:- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-517-4028/8025
ኢ-ሜይል: AynalemAy@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
