በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ለደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት ለመንገድ ጥገና አገልግሎት የሚውል ጋቢዮን ቦክስ (ጋቢዮን ሳጥን) በሀገር ውስጥ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ቲ 04-2017
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ለደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት ለመንገድ ጥገና አገልግሎት የሚውል ጋቢዮን ቦክስ (ጋቢዮን ሳጥን) በሀገር ውስጥ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
በአቅራቢዎች ዝርዝር ያልተመዘገቡ ተጫራች ለሚመለከተው መንግስት መ/ቤት በማመልከት የምዝገባ ሰርተፍኬት ማግኘት ይቻላል፡፡
1. የዕቃ ማስረከቢያ ቦታ ደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት ዕቃ ግምጃ ቤት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋርየተዛመደ ንግድ ስራ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እና በጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ በማቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በኢ.መ.አ. ንግድ ባንከ አካውንት ቁጥር 1000322269165 በመከፈል ደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት ግዥና አቅርቦት ቡድን ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይቻላል፡፡
2. የጨረታ አሸናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ከፍት ነው፡፡ የጨረታ ሠነድ የተዘጋጀው በአማረኛ ቋንቋ ነው፡፡
3. አቅራቢዎች ጨረታውን በዲስትሪከቱ ግዥና አቅርቦት ቡድን ቢሮ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ የሚያደርጉት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ቀናት አየር ላይየሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡
4. ተጫራቾች ከብር 50,000.00 ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በገንዘብ ያዥ በተፃፈ ቼክ ወይም የባንከ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ ከሰነዶቻቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚያቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ16ኛው ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት በደ/ማርቆስ መ/ጥገና ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ከሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ሆኖም ቀኑ በበአል ወይም በእሁድ ምክንያት ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾች በጨረታ ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው መመሪያ ውጭ የሚያቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
7. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
8. ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይቻላል፡፡
ስልክ ቁጥር 0587713052/0911984416/09129049751
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ግዥና አቅርቦት ቡድን
