በየካ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን በ2018 በጀት ዓመት ከ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ለሚያካሂደው ጥቅል ግዥመሳተፍ የምትፈልጉ ሀጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት አንድትጫረቱ ይጋብዛል።
በየካ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር የካT/ሰ/ጽ/ቤት 001/2018
በየካ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን በ2018 በጀት ዓመት ከ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ለሚያካሂደው ጥቅል ግዥ
ሎት 1. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት2 የጽዳት እቃ ሎት 3. የደንብ ልብስ ሎት 4. ህትመት ሎት5.ውሀ ቆሎ የአገልግሎት (መስተንግዶ) ሎት6. ድንኳን ከራይ ሎት 7. የመኪና ጌጣጌጥ፣ ሎት 8. የመኪና ክራይ ሎት 9. የቧቧና ኤሌከትሮኒክስ እቃዎች ሎት 10. የተሌብዥንና የሬዲዮ ማስታወቂያ ሎት11. ኤሌከትሮኒክስ እቃዎች ሎት 12. የሙዚቃ መሳሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ሀጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት አንድትጫረቱ ይጋብዛል።
ከተጫራቾች በሚሳተፉበት የግዥ ዓይነት በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀትና የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2.የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ናሙና እንዲያቀርቡ የተጠየቁባቸውን እቃዎች መጫረቻ ሰነዳቸውን ሲያስገቡ አብረው የተጠየቀውን ወይም የሚወዳደሩበትን ናሙና የማስገባት ግዴታ አለባቸው።
4.የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ከሚመለከተው የገቢ ግብር ባለስልጣን ከሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1፣ ሎት 2፣ ሎት 4፣ እና ሎት 5፣ ለእያንዳንዳቸው 5.000.00 (አምስት ሺብር) ሎት3. 6,000 (ስድስት ሺብር) ሎት6፤ ሎት7፣ ሎት8 'ሎት9 ፤ ሎት10፣ ሎት11፡ሎት12፡ ለእያንዳንዳቸው 10,000 (አስር ሺ ብር) በየካ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ በባንክየተረጋገጠ ሲፒኦ ወዘተ ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሚገባ በመሙላት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይየሥራ ቀና ውስጥ በሥራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያየ ኤንቨሎፕ በማድረግ ዋና እና ኮፒ መሆኑን በመግለዕ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. የጨረታ ሳጥኑ በ 11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 7ኛ ፎቅ በሚገኘው የመንግስት ግዥ ቡድን ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።
9.ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበት እና ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል። የቀረበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑና አለመሆኑ ካልተገለፀ የቀረበው ዋጋ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
10.ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን ያላሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም ።
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉበሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡-መገናኛ ማራቶን ሕንፃ ሬትሰፊት በሚገኘው የየካ ከፍስ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 7ኛ ፎቅ
ስልክ፡ 0118931900/0910547564
በየካ ክፍስ ከተማ አስተዳደር ፐብሲክ ሰርቪስና
የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት
