የሰበታ መርሐ ዕውራን 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ለተማሪዎች በ2018 መደበኛ በጀት የተለያዩ የምግብ አይነቶችን፣ ስቴሽነሪ፣ የተማሪ ደንብ ልብስ፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ ማገዶ(ግንድላ) እና የደንብ ልብስ ስፌት ለማቅረብ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሰበታ መርሐ ዕውራን 1ኛ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የሰበታ መርሐ ዕውራን 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ለተማሪዎች በ2018 መደበኛ በጀት የተለያዩ የምግብ አይነቶችን፣ ስቴሽነሪ፣ የተማሪ ደንብ ልብስ፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ ማገዶ(ግንድላ) እና የደንብ ልብስ ስፌት ለማቅረብ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
1. የተዘጋጀውን የምግብ እና ከላይ ዝርዝር የያዘ የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ የማይመለስ ብር 150.00 በመከፈል ከት/ቤቱ ሂሣብና በጀት ቢሮ ቁጥር 4 መውሰድ ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች በተጠቀሱት ዕቃ አይነቶች የንግድ ፈቃድ ያላቸውና በ2017 ዓ.ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የዘመኑን ግብር የገበሩ፣ የቫት ተመዝጋቢና ከላይ የተጠቀሱትን የዕቃ ዝርዝርዓይነቶች አቅራቢነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚገልፅ የምስከር ወረቀት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሣጥን ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ አቅርቦት ለሚከፍሉበት ንግድ ዘርፍ በጥሬ ብር ወይም በቼh 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በት/ቤቱ የባንክ ሂሣብ ቁጥር 1000016086006 ገቢ በማድረግ በካሽ ወይም በCPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን ከላይ የተጠቀሱትን የዕቃ ዝርዝሮች በገዙት የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ላይ የሚያቀርቡበትን ዋጋ ግልጽ በሆነ የእጅ ጽሑፍ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በተጫራቹ ድርጅት ማህተምና በድርጅቱ ኃላፊ/ተጫራቹ ፊርማ /ተረጋግጦ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ቢሮ ቁጥር 2 ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
5. ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 2 ውስጥ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፤ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
6. በዚህ ጨረታ አሸናፊ የሆነው ተጫራች/ድርጅት/ የሚያስገባውን የተጠቀሱትን የዕቃ ዝርዝርዋጋ አስር በመቶ (10%) የማስያዝ ግዴታ አለበት፡፡
7. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፤
ሥጋ ፣ ዳቦ፤ የጤፍ ዱቄት ከሰበታ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113380006 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የሰበታ መርሐ ዕውራን 1ኛ ደረጃ ት/ቤት
