በሀዲያ ዞን ምዕራብ ባደዋቾ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች (መኪናዎች፣ ሞተር ሳይክሎች፤ ጀነሬተር እና ወተር ፓምፕ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በሀዲያ ዞን ምዕራብ ባደዋቾ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በሀዲያ ዞን ምዕራብ ባደዋቾ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች (መኪናዎች፣ ሞተር ሳይክሎች፤ ጀነሬተር እና ወተር ፓምፕ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳትፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
ሎት - 1 መኪናዎች፣
ሎት - 2 ሞተር ሳይክሎች፣
ሎት - 3 ጀነሬተር፣
ሎት - 4 የውሃ ፓምፕ
1. ተሸከርካሪዎቹ ወይም ማሽነሪዎች የሚገኙበት አድራሻ በሀዲያ ዞን ምዕራብ ባደዋቾ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛሉ፡፡
2. በተሸከርካሪዎች ጨረታ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ ይችላል፡፡
3. ተጫራቾች ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም እና የተጫራቾች መመሪያ ጋዜጣው አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በተከታታይ 21/ሃያ አንድ ቀን፣ ቀናት ውስጥ በእያንዳንዱ ተሸከርካሪ በተናጠል፡- ሎት - 1 መኪና ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/፣ ሎት- 2 ሞተር ሳይክል ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ ፣ ሎት - 3 ጀነሬተር ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ እና ሎት – 4 የውሃ ፓምፕ ብር200.00/ሁለት መቶ/ የማይመለስ ብር በመከፈል በሀዲያ ዞን ምዕራብ ባደዋቾ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 05 በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
4.ተጫራቾች የሚወዳደሩትን ተሸከርካሪዎች እና ማሸነሪዎች በሎት በተናጠል ወይም በድምር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የመነሻ ዋጋ 20% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
5. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ መሙያ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 /ሃያ አንድ ቀን/ ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታ አንድ ዋና /Original/ እና ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻ በፖስታ ታሽጎና እንደገና ሁለቱም በአንድ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 05 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ዋጋውን በግልጽ በአሃዝና በፊደል በመጻፃፍ በእያንዳንዱ በቀረበው ዋጋ ፊት ለፊት በፊርማ ማረጋገጥ አለባቸው ያልተፈረመ ሰነድ ዋጋ አይኖረውም፡፡
7. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሠረት ከአንድ በላይ ተሽከርካሪ ወይም ማሽነሪ መጫረት ይችላሉ፡፡
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22ኛው/ሃያ ሁለተኛ/ ቀን በ8፡00 ሰዓት ላይየጨረታ ሳጥን ታሽጎ ሰ8፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
9. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪዎች ወይም ማሸነሪዎች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ በተገለጸ 10/አስር/ የሥራ ቀናት ውስጥ ማንሳት አለባቸው ሆኖም በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ገዢው ካላነሳ ለሚደርሰው ለማንኛውም ችግር ሻጭ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
10. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪዎች ወይም ማሽነሪዎች ከመንግሥት የሚፈለግ ግብርና ቀረጥ በሻጩ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
11. አሸናፊው ተጫራች ተሸከርካሪዎች ወይም ማሸነሪዎች ስም ማዘዋወሪያ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ወጪዎች በሙሉ በአሸናፊው ይሸፈናል፡፡
12. ተጫራቾች የመነሻ ዋጋ እና የዋጋ ማቅረቢያ የጨረታ ሰነድ አካል ሲሆን ከጨረታ ሰነድ ጋር የተያያዘ ነው፡፡
13. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0926118228/ 0912116603/ 0978898435/
0912417950/ ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻስን፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በሀዲያ ዞን ምዕራብ ባደዋቾ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
