በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ አልባሳትና ቁሳቁሶች አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 6 የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ አልባሳትና ቁሳቁሶች አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ዋጋው በአንድ ላይ በጥቅል በመሙላት የሚወዳደሩ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ መነሻ ዋጋ 187,753 ብር (አንድ መቶ ሰማንያ ሰባት ሺ ሰባት መቶ ሀምሳ ሶስት) ተጫራቾች ይህንን ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጨረታ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታ 5 ቀናት በአስቸኳይ የጨረታ ሰነድ ከወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ቀርበው 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ፡፡
አድራሻ ቄራ ገብርኤል 100 ሜትር ገባ ብሎ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ 5000 ብር (አምስት ሺ ብር) አያይዛችሁ ማቅረብ አለባቸሁ፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸሁን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት አንስቶ ለ5 የስራ ቀናት ቄራ ጎፋ ገብርኤል 100 ሜትር ገባ ብሎ በወረዳ 06 አስተዳደር ንብረት አስተዳደር ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ንብረቶቹ በዝርዝር ን/ስ/ላ/ክ/ወረዳ 06 አስተዳደር ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ በ6ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 3፡10 ሰዓት በወረዳ 06 አስተዳደር ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ሳጥኑ ይከፈታል፡፡
አሸናፊው ድርጅት ካሸነፈበት ቀን በተከታታይ በ5 የስራ ቀን ውስጥ ክፍያ በመፈፀም ዕቃውን ካላነሳ ያስዘውን ሲፒኦ ተወርሶ ሁለተኛ ለወጣው ይሰጣል፤ ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 6 የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት
