በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ ንብረትነቱ በኦሮሚያ ጤና ቢሮ የኡራጋይ ሆስፒታል የሆኑ በቦረና ዞን ኡራጋይ ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency (የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ)
ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 02/2018
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ ንብረትነቱ በኦሮሚያ ጤና ቢሮ የኡራጋይ ሆስፒታል የሆኑ በቦረና ዞን ኡራጋይ ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ በጷጉሜ 3/2017 ዓ.ም ድረስ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን፤
- የኤጀንሲው አድራሻ አዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ/የኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ጫፌ አናኒ ህንጻ ከሚገኘው የኤጀንሲው የግዢ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3rd Floor) ቢሮ ቁጥር-03 በመቅረብ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ከየመንግስት ንብረት ዋጋ ግምትና ሽያጭ ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3rd Floor) ቢሮ ቁጥር -02 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 6፡30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7:30 - 10:30 ሰዓት ብቻ ነው:
- የንብረቶቹን ሁኔታ እስከ በጷጉሜ 3/2017 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 11፡00 ሰዓት ድረስ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለፀው ቦታ በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ በጷጉሜ 4/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ድረስ በኤጀንሲው ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በጷጉሜ 4/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ5፡15 ተዘግቶ በዕለቱ በ5፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለያንዳንዱ ጨረታ መናሻ ዋጋ 25% /ሃያ አምስት በ100/ የጨረታ ማስከበሪያ C.P.O በማዘጋጀትና ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
CPO ለማሰራት
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-1-8340-636
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ
ፊንፊኔ
