አጋርፋ የግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምርትና ሥልጠና ኮሌጅ የሚከተሉትን ዕቃዎች:- የአረም መከላከያ መድኃኒት (ኬሚካል)፤ የተባይ መከላከያ መድኃኒት (ኬሚካል) እንዲሁም የግብርና ኬሚካል መርጫ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Agarfa Agricultural Technical Vocational Educational & Training College (አጋርፋ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ)
የዕቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር - 01/001/2018
አጋርፋ የግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምርትና ሥልጠና ኮሌጅ የሚከተሉትን ዕቃዎች:- የአረም መከላከያ መድኃኒት (ኬሚካል)፤ የተባይ መከላከያ መድኃኒት (ኬሚካል) እንዲሁም የግብርና ኬሚካል መርጫ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን መመሪያዎችንና ግዴታዎችን በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡ ጨረታው የሚከናወነው በግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ባወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ መሠረት ብቁ ለሆኑ አገሮች ተጫራቾች ነው።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ:-
- ከመስኩ ጋር አግባብነት ያለውና የታደሰ (የእድሳት ጊዜው ያላለፈበት) የሥራ/የንግድ ሥራ ፈቃድ፤
- የግብር ክፍያ የምስክር ወረቀት/TIN/፤
- እንዲሁም እንደ አስፈላጊነቱ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤
- e-gp ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- በመንግስት የግብር ሕግ መሠረት ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡና መንግስት በሚያወጣቸው ጨረታዎች ላይ መሳተፍ የሚችሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ጊዜው ያላለፈበት የድጋፍ ደብዳቤ /የምስክር ወረቀት/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገቡበትን ቅጽ በመሙላትና በመፈረም ከሚያቀርቡት የዕቃዎች አገልግሎቶች/ ዋጋ ዝርዝር ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ዕቃ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል በጨረታ ሰነዱ ክፍል 2 የጨረታ ዝርዝር መረጃ ሠንጠረዥ ውስጥ እና በጥቅል መረጃ ውስጥ የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያሰተመሠረተ የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ዋስትና /CPO/ በአጋርፋ የግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ ስም አዘጋጅቶ ማቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸለት በ10 /አስር/ ቀናት ውስጥ የውል ስምምነት ካልፈፀመ ፈቃደኛ እንዳልሆነ ተቆጥሮ ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለኮሌጁ ገቢ ይሆናል፡፡
- በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ሕጋዊ ተወዳዳሪዎች በአንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ብቻ በጥሬ ገንዘብ በሕጋዊ ሰነድ በመክፈል አዲስ አበባ ኃይሌ ገ/ሥላሴ ጎዳና በጌታሁን በሻህ ሕንፃ በኩል ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ከአዲስ ሕይወት ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው አላጌ የግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ ጉዳይ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሚገኘው የአጋርፋ ኮሌጅ ጉዳይ አስፈፃሚ ጽ/ቤት እና አጋርፋ የግ/ቴ/ሙ/ት/ትና ሥ/ኮሌጅ ግዥና ፋይናንስ ሥራ አስፈጻሚ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ይህ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከመጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ የዋጋ ማቅረቢያቸውን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለያየት ከተያያዥ ሰነዶች ጋር በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ አዲስ አበባ የኮሌጁ ጉዳይ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን፡-
- የአረም መከላከያ መድኃኒት (ኬሚካል)፣ የተባይ መከላከያ መድኃኒት (ኬሚካል) እንዲሁም የግብርና ኬሚካል መርጫ መሳሪያዎችን ነሐሴ 19 ቀን 2017 ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ የኮሌጁ ጉዳይ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
- ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ ይችላል፡፡
ለበለጠ መረጃ-
ስልክ ቁጥር፡- 0116625004 አዲስ አበባ
0910316003/0922565819/ አጋርፋ ኮሌጅ
ፋክስ ቁጥር- 0221191164 አጋርፋ ኮሌጅ
ፖስታ ሳ.ቁ- 15/211 ባሌ ሮቤ
አጋርፋ የግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምርትና ሥልጠና ኮሌጅ
