ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ ብረታ ብረቶችን እና የተለያየ መጠን ያላቸው የመኪና ባትሪዎች ባለባት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
BEAEKA General Business PLC (ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር)
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ ብረታ ብረቶችን እና የተለያየ መጠን ያላቸው የመኪና ባትሪዎች ባለባት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጸው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች እቃዎቹን ከሚሸጡበት ቦታ በራሳቸው ወጪ አንስተው መውሰድ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚያስገቡትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከነሀሴ 5/2017 ዓ.ም እስከ ነሀሴ 20/2017 ዓ.ም ድረስ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጥዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጥዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ማስገባት ይቻላል።
- ተጫራቾቹ ለሽያጭ የተዘጋጁትን እቃዎች አዲስ አበባ ሃና ማሪያም ኢንዱስትሪ ግንባታ ፕሮጀክት ቅጥር ግቢ ውስጥ መመልከት ይችላሉ።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል አዲስ አበባ ሃናማርያም አስተዳደር እና ጠ/አገልግሎት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለሚያቀርቡት የጠቅላላ ዋጋ 5 ፐርሰንት በ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሃሴ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከጧዋቱ 4፡00 ሠዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን በ5፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ሃናማርያም በሚገኘው አስተዳደር እና ጠ/አገልግሎት ቢሮ ይከፈታል።
- ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 0905050189/0930363880
ድርጅቱ
