የኢትዮ ኮምፔንሳቶ እና እንጨት ማቀነባባሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሲገለገልባቸው የነበሩ ከዚህ በታች የተገለፁትን ንብረቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
Ethio Plywood & Wood Processing Plc (የኢትዮ ኮምፔንሳቶ እና እንጨት ማቀነባባሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር)
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮ ኮምፔንሳቶ እና እንጨት ማቀነባባሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሲገለገልባቸው የነበሩ ከዚህ በታች የተገለፁትን ንብረቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች ንብረቱ በሚገኝበት አድራሻ በመቅረብ በጨረታው ላይ እንዲወዳደሩ ተጋብዟል፡
- ተጫራቾች በተናጠል ለሚወዳደሩበት ንብረት እና የጨረታ ማስከበሪያ /Bid Bond/ በባንክ ክፍያ ማዘዝ /CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ሎት አንድ ያገለገሉ በስራ ላይ ያሉ ኮምፔንሳቶ ማሽኖች እና ካተርፒለር ጀኔሬተር
- ሎት ሁለት ያገለገሉ ማሽኖችና ተጓዳኝ ዕቃዎች
- ሎት ሶስት አዳዲስ የዶዘር መለዋወጫ ዕቃዎች
- ሎት አራት ያገለገሉ ብረታ ብረቶች፣ የብርጭቆ ወረቀት፣ እና እስቴፕለር ሽቦ
- ሎት አምስት ያገለገሉ የቤት እና የቢሮ እቃዎች፣
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሚጫረቱበት ዋጋ 2% /ሁለት በመቶ/ በባንክ የተረጋገጠ ክፍያ ሰነድ /CPO/ በማቅረብ መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከፋብሪካው መግዛት ይችላሉ፤
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ /ማሻሻያ/ ማድረግ እና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፤ ተጫራቾች በአንድ ወይም ከአንድ በላይ በሆነ ሎት ላይ መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ ሙሉ ስም እና አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፤
- ተጫራቾች በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፤
- ተጫራቾች በጨረታ የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ ኦርጅናል ኮፒ በማለት በሁለት የተለያየ ኤንቬሎፕ ውስጥ በማሽግ ይህ ማሰታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ንብረቶችን በአካል በመመልከት ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 2 ማስገባት ይችላሉ፤
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጧዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል። የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፤
- አሸናፊው የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና አስይዞ ውል በመፈረም ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ከፍሎ እንዳጠናቀቀ ንብረቶቹ በ5 ቀናት ውስጥ ይረከባል በእነዚህ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ከፍሎ ንብረቶቹን ካልተረከበ ያስያዘው ዋስትና ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።
- ከላይ የተዘረዘሩት የሚሸጡ ዕቃዎች ላይ የተ.እ.ታ ይታሰባል::
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመስረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
የኢትዮ ኮምፔንሳቶ እና እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
አድራሻ፡- ጦር-ኃይሎች ከአውጉስታ ወይራ ቤቴል
በሚወስደው መንገድ ላይ ፂሆን ማርያም ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ለተጨማሪ መረጃ
በስ.ቁ 011 371 15 60
ሞባይል 09 40 25 90 65 / 09 79 09 77 46
