የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት መሰረት ለፈርኒቸር ምርት ሥራ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የብረት ግብዓቶች ግዥ ለመፈጸም ብቃት ያላቸው አምራች እና አከፋፋይ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Educational Materials Production and Distribution Enterprise (የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ግልጽ ጨረታ ቁጥር EMPDE/NCB/04/2017
የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት መሰረት ለፈርኒቸር ምርት ሥራ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የብረት ግብዓቶች ግዥ ለመፈጸም ብቃት ያላቸው አምራች እና አከፋፋይ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ነጥቦች ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
1. በዘርፉ ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የታክስ ከሊራንስ ደብዳቤ፤ የተ.እ.ታ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ ግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና የአቅራቢ ምዝገባ ሰርተፍኬት መሆኑን።
2. ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 600 /ስድስት መቶ ብር/ በመክፈል ከትም/መሳሪ/ማም/ማከ/ድርጅት ዘወትር በሥራ ሰዓት ጠዋት 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት እንዲሁም ከ7፡30 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 35 መውሰድ ይችለሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንከ ጋራንቲ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
4. ጨረታው ነሐሴ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡
5. ከላይ የተዘረዘሩትንና በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተመለከቱትን ግደታዎች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የድርጅቱ አድራሻ፦ ከመገናኛ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መንገድ ከሆሊ ሲቲ ሴንተር ህንጻ ሲደርሱ ወደ ቀኝ ታጥፎ ይገኛል፡፡
ለበለጠ መረጃ Tel. /0116 -46-34 81 መረጃ ማግኘት ይቻላሉ፡፡
