የባቱ ከተማ ገንዘብ አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 የበጀት አመት አዲስ ለተገነባው የሕዝብ ስብሰባ አዳራሽ የሚያገለግል-1ኛ- የአዳራሽ ወንበሮችና የተለያዩ ኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የባቱ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
የአዳራሽ ወንበር ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
የባቱ ከተማ ገንዘብ አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 የበጀት አመት አዲስ ለተገነባው የሕዝብ ስብሰባ አዳራሽ የሚያገለግል-1ኛ- የአዳራሽ ወንበሮችና የተለያዩ ኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ በጨረታ ለመሳተፍ የም የምትፈልጉ ተጫራቾች ባቀረባችሁት የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ በመ መሙላት እንድትወዳደሩ የተጋበዛችሁ ስለሆነ ያሸነፉትን ዕቃ እስከ ባቱ/ዝዋይ ከተማ ገንዘብ አስተዳደር ጽ/ቤት ከተማ ድረስ ያቀርቡበትን የመጓጓዣ የማስጫኛ እና የእጅ ስራንና ማውረጃ ወጪውን በመጨመር ከዚህ በታች በተጠቀሰው መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል፡፡
1ኛ-ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
2ኛ-በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ _ በሚጫረቱበት ዘርፍ የተመዘገቡ ስለመሆኑ ማስረጃ የሚያቀርብ፡፡
3ኛ-ተጫራቾች የንግድ ስራ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብና የግብር ከፋይነት መለያና ቫት(VAT) ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒ _ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4ኛ-የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-11፡30 ሰዓት ድረስ የሚሸጥ መሆኑን፡-
5ኛተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ 500( አምስት መቶ ብር ብቻ ) ለሰነድ ግዥ በመከፈል ከመ/ቤታችን የግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ከፍል መግዛት የሚችሉ መሆኑን፡፡
6ኛ-ተጫራቾች ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO)ብቻ በባቱ/ዝዋይ ከተማ ገ/አስተዳደር ጽ/ቤት ስም አስገብቶ ከጨረታ ሰነድ ፋይናንሻል ኦሪጅናል ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
7ኛ-ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ የዋጋ ሰነድ በጥራት ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመስሪያ ቤቱ ጥያቄ መሰረት ብቻ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻውንና የተወዳደሩትን ዕቃ አይነት በመጥቀስ ከ4/12 /17 እስከ 25/12/17 ሰዓት 8:00 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡-
8ኛ-ጨረታው በ25/12/17 ከሰዓት 8፤30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት/ባይገኙም በባቱ ከተማ ገ/አስተዳደር ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ከፍል ይከፈታል፡፡
9ኛ-ተጫራቾች ሙሉ መረጃውን ከሰነዱ ላይ ታገኛላችሁ፡፡
10ኛ-ጽ/ቤቱ የተሻለ/አማራጭ/መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብት በህግ የተጠበቀ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ስበስጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-45-38-94-44/0911-51-02-44/ ደውለው ይጠይቁ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በበዓልና በዝግ ቀናት ላይከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን ላይ ይሆናል፡፡
የባቱ ከተማ ገንዘብ አስተዳደር ጽ/ቤት
