በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ እና በሥሩ ለሚገኙ ሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን ሲሲቲቪ ካሜራ ከነዝርጋታው ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ እና በሥሩ ለሚገኙ ሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን ሲሲቲቪ ካሜራ ከነዝርጋታው ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል በዚህም መሠረት፡-
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ሆነው በሥራ መስኩ የተሰማሩ ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ በሙያው የተሰማሩ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ ሲፒኦ /CPO/ በመ/ቤታችን ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ለአንድ ሎት የማይመለስ 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ ጀሞ ሚካኤል መስቀለኛ መንገድ የግዥ ቢሮ ቁጥር 503 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ ጀሞ ሚካኤል መስቀለኛ መንገድ አጠገብ ካለው ሕንፃ የግዥ ቢሮ ቁጥር 503 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
- ጨረታው በአስረኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በፖሊስ መምሪያው የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሑድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች መ/ቤቱ መመዘኛ መስፈርት /Specification/ ባወጣንባቸው ዕቃዎች ላይ ሌላ የራስን መመዘኛ /Spec/ አውጥቶ መወዳደር አይቻልም ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ድረስ ማቅረብ እና የዝርጋታ እና የመገጣጠም ሥራ ሠርቶና አጠናቆ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ለውል ማስከበሪያ 10% ዋስትና መስጠት ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ
አድራሻ ን/ስ/ላ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ ጀሞ ሚካኤል መስቀለኛ መንገድ አጠገብ በስልክ ቁጥር 0114423315/ 0114431529/ 0118334107/ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የን/ስ/ላ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ
