ኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ አንደ (1) የሆኑ የአገር ውስጥ እና የአገር ውስጥ ፈቃድ ያላቸው ዓለም አቀፍ የመንገድ ሥራ እማካሪ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የዶሎ አዶ እየር ማረፊያ የምህንድስና ዲዛይን፣ የጨረታ ሰነድ ዝግጅት፣ የኮንስትራክሽን ቁጥጥር እና የኮንትራት አስተዳደር ሥራ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: SSNT-T554
ኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ አንደ (1) የሆኑ የአገር ውስጥ እና የአገር ውስጥ ፈቃድ ያላቸው ዓለም አቀፍ የመንገድ ሥራ እማካሪ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የዶሎ አዶ እየር ማረፊያ የምህንድስና ዲዛይን፣ የጨረታ ሰነድ ዝግጅት፣ የኮንስትራክሽን ቁጥጥር እና የኮንትራት አስተዳደር ሥራ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-
1. ፕሮጀክቱ በሶማሌ ከልል ሊበን ዞን በዶሎ አዶ ከተማ ይገኛል።
2. አማካሪነት አገልግሎት ሥራው ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ዲዛይን በ5 ወራት ውስጥ ለግንባታ ቁጥጥር እና ኮንትራት አስተዳደር በ15 ወራት ውስጥ ማጠናቀቅ እና አንድ ዓመት ክትትል ጊዜ (Defect liability period) ይሆናል::
3. ለሥራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግሥት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች ከኢትዮጵያ ኮንስትራከሸን ባለሥልጣን ለ2017 ዓ.ም የታደሰ በመንገድ ሥራ ማማከር አገልግሎት ደረጃ-1 የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T554 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ፣ የድርጅቱን ስም እና ስልከ ቁጥር ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ከፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንከ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡
7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴከኒካል ከፍል እስከ ነሐሴ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መከፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ፡-
ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መሥሪያ ቤት
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ስልክ ቁጥር: +25111-517-89-18
ኢ-ሜይል: ESAYASTS@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሱ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
