የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የክልል ኤርፖርቶችን (ጂንካ ፡ ጎዴ ፡ አክሱም ፣ አርባ ምንጭ ፡ ቀብሪ ደሓር፣ ላሊበላ ፣ ጋምቤላ) ሴክዩሪቲ አጥር ግንባታ ሥራ የሚያከናውን ደረጃ አንድ (1) ጠቅላላ ወይም ህንፃ ስራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: - SSNT-T555
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የክልል ኤርፖርቶችን (ጂንካ ፡ ጎዴ ፡ አክሱም ፣ አርባ ምንጭ ፡ ቀብሪ ደሓር፣ ላሊበላ ፣ ጋምቤላ) ሴክዩሪቲ አጥር ግንባታ ሥራ የሚያከናውን ደረጃ አንድ (1) ጠቅላላ ወይም ህንፃ ስራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ፕሮጀክቱን የማጠናቀቂያ ጊዜ ሥራው ከተጀመረበት በ180 ቀናት ውስጥ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
1. ተጫራቹ ለ2017 ዓ. ም የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርቲፊኬት (TIN) ማቅረብ የሚችል እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
2. በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ከሚሰጥ ሕጋዊ አካል ለ2017 ዓ.ም የታደሰ ደረጃ አንድ ጠቅላላ ወይም ሕንፃ ሥራ ተቋራጭ የሆነ ፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
3. የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ከታከስ እዳ ነጻ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
4. የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ውስጥ ለመሳተፍ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተሰጠ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰላሳ (30) ተከታታይየሥራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (ብር100.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T555 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (scan copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
6.በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት አምስት መቶ ሺህ ብር (500,000.00ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው (Conditional) የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጨረቻ ሠነዳቸውን (ቴከኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ከፍል እስከ ጳጉሜ 04 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል የጨረታ መከፈቻ ከፍል በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፦
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ ስስም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መሥሪያ ቤት
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
አቶ አሲ አስፋው
ስልክ ቁጥር: 011-517-4552
ኢ-ሜይል: AliAs@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻስ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሱ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
