በሸገር ከተማ አስተዳደር የሲዳ አዋሽ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለወረዳው አገልግሎት የሚውሉ ፒካፕ (pick-up) መኪና መከራየት ይፈልጋል::
በሸገር ከተማ አስተዳደር የሲዳ አዋሽ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በሸገር ከተማ አስተዳደር የሲዳ አዋሽ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለወረዳው አገልግሎት የሚውሉ ፒካፕ (pick-up) መኪና መከራየት ይፈልጋል::
በዚህም መሰረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን በማሟላት በጨረታው እንዲሳተፍ ይጋብዛል::
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑ ግብር የከፈሉ።
2. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT), TIN ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ያላቸው::
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት 15(አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ለአንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በሲዳ አዋሽ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በመከፈል ሰነዱን ከሲዳ አዋሽ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር (ሰነድ) ዋና እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፖስታ/ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15(አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ በሲዳ አዋሽ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
5. በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ(ተዘግቶ) ልከ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሲዳ አዋሽ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል።
8. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውል ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካልስያዙ የጨረታ ማስከበሪያው ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
9. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም መሻሻል ወይም ጨረታው ትቻለሁ ማለት አይቻልም።
10.የመወዳደሪያ በጨረታ ሰነዱ በተዘረዘረው መሠረት ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል።
11.የመንግስት ፋይናንስ ህግ እና መመሪያን የሚጥስ ማንኛውም ነገር ተቀባይነት የለውም።
12.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13.ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0985815867/0941340508 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
ገሳን ክፍስ ከተማ የሲዳ ስዋሽ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
