Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የምስ/ሐ/ዞን የባቢሌ ከተማ ገ/ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት በከተማው ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚሆን የተለያዩ የማሰልጠኛ እቃዎች እና አላቂ እቃዎች የጽህፈት መሣሪያ፣ የደንብ ልብስ የተለያዩ ቋሚ እቃ እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ የሞተር ሳይክል እና መኪና መለዋወጫ ዕቃዎች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የባቢሌ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የምስ/ሐ/ዞን የባቢሌ ከተማ ገ/ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት በከተማው ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚሆን የተለያዩ የማሰልጠኛ እቃዎች እና አላቂ እቃዎች የጽህፈት መሣሪያ፣ የደንብ ልብስ የተለያዩ ቋሚ እቃ እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ የሞተር ሳይክል እና መኪና መለዋወጫ ዕቃዎች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ የጨረታው መስፈርት

  1. ተጫራቾች የፅህፈት መሣሪያ፣ የደንብ ልብስ፣ የተለያዩ ቋሚ እቃ እና የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች የሚገልጽ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የአቅራቢነት ምዝገባ ወረቀት ያላቸውና የዘመኑን ግብር ያጠናቀቁ ወይም ከገቢዎችና ጉምሩከ ባለሥልጣን ክሊራንስ እንዲሁም የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የተለያዩ የጨረታ እቃዎችን ዝርዝር የሚገልጽ የጨረታውን ሰነድ ጨረታው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታዩ አስራ አምስት (15) ባሉት የስራ ቀናት ውስጥ ከባቢሌ ከተማ ገ/ጽ/ ቤት የማይመለስ ብር 300.00 በመክፈል ጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፤፤
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አጠቃላይ ሰነድ ቢድ ቦንድ ብር 30,000.00 በባንክ የተረጋገጠ CPO ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በባቢሌ ከተማ ገ/ፅ/ ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እና ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ይከፈታል ተብሎ በተቀመጠው ቀን ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈውን ዕቃ በሚደረገው ስምምነት መሠረት በራሱ ትራንስፖርት እስከ ባቢሌ ከተማ ገ/ ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች ጨረታ በሚከፈትበት ቀን በጨረታው ውስጥ የተጠቀሱትን የኮምፒውተር ቀለም፣ ኮምፒውተር ወረቀት፣ ፎቶ ኮፒ ቀለም፣ ደንብ ልብስ፣ ስክሪፕቶ የወንድና የሴት ጫማ ዓይነት ለናሙና አንድ አንድ ፍሬ ማምጣት ይኖርባቸዋል።
  8. የጨረታው ሰነድ ስርዝ ድልዝ ያለው ከሆነ ከጨረታ ውጪ ይሆናል።
  9. የጨረታ ሣጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
  10.  ተጫራቾች የገዙት እያንዳንዱ ሰነድ ገጽ ላይ ማህተምና ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡
  11.  ተጫራቾች ስለሚያቀርቡት እቃ የጥራት ደረጃ ጥራቱ ከሀገር ውስጥ ጥራት ደረጃ የተረጋገጠ መሆን አለባቸው፡፡
  12.  መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መሰል የተጠበቀ ነው፡፡
  13.  የመንግሥት ግዥ ቅጣቶች፡- ተጫራቹ ከዚህ ቀደም ከሕዝብ ግዥ ያልታገዱ ወይም ያልተከለከሉ ለመሆኑ በፌዴራል ወይም BMO ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በሚቀርብ ማስረጃ ወይም በድህረ ገጽ የሚታይ ይሆናል፡፡ ማሳሰቢያ: መስሪያ ቤቱ አሸናፊውን ለመለየት በጥቅል ወይም በእያንዳንዱ ዋጋ ላይ ተመስርቶ ሊያወዳድር ይችላል፡፡ ለተጨማሪም መረጃ በስልከ ቁጥር 0921-84 50-53/ 0922-90 3950 በስራ ሰዓት ይደውሉ፡፡

                                  

የባቢሌ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት

                                          

 

Save Tender