የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከዚህ በታች የተመለከተውን፤
- ሎት 1 የመዋኛ ገንዳ ሞዛይክ ሽክላ 450 ካሬ1 100 ከረጢት አግሬሲቭ እና የመዋኛ ገንዳ ፓምፕ ብዛት 3
- ሎት 2 የጄኔሬተር ኬብል ዋየር 3*300 mm/150 mm ብዛት 30 ሜትር
- ሎት 3 አውቶማቲክ ኮንትሮል ቦርድ A/T/S 1250 AP
- ሎት 4 (Air conditioner) የሙቀት መከላከያ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች በዝርዝር የተመለከቱ ሁኔታዎችን በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡-
- ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ በተረጋገጠ CPO 20,000.00 (ሃያ ሺህ) ብር ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ብር ብቻ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000342552424 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ የታደሰ ንግድ ፈቃድና ተያያዥነት ያላቸው ሰነዶች ኮፒ ይዞ በመቅረብ ከግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 310 ቀርበው ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ከተውና በሁሉም ዶክመንት የድርጅቱን ማህተም በመምታትና በመፈረም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 እስከ 8፡30 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት 9፡00 ላይ ይከፈታል ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፉበትን ዕቃ እስከ ሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ቢሮ በማቅረብ ያስረክባል/ይገጥማል ።
በተጨማሪም አሸናፊው ድርጅት አስቀድሞ የዕቃውን ናሙና ማቅረብ፣ ማሳየትና ከቢሮው ጋር መተማመን ይኖርበታል ፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል ፡፡
ዝርዝር የጨረታ ሂደት በጨረታው ሰነድ መመሪያ ላይ ተገልጧል። ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0462124290/91
የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
