Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ሽሮሜዳ ከስላሴ ቤተክርስቲያን በታች ባለው በግራ በኩል መታጠፈያ 500 ሜትር ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0111-22-67-04
  • Website
  • Deadline12 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያ የብር መጠኑ በየአገልግሎቱ የተለያየ ነው።
  • opening date2025-08-13 00:00:00
  • Categories Printing And Publishing , Catering And Cafeteria Services , Transportation Service And Cargo

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥው መለያ ቁጥር 001/2018

 

  1. የካፍቴሪያና የመስተንግዶ አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 129,768.00 ብር
  2. የትራንስፖርት አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 21,100.00 ብር
  3. የህትመት አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 37,240.00 ብር

በጨረታው ለመካፈል ተጫራቾች

1ኛ. በጨረታ የሚወደዳሩ ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት በስማቸው ያላቸውን የዘመኑን ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የግብር ግዴታቸውን በግብር አስገቢ ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ የሚያቀርቡ

2ኛ. ተጫራቾች የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /TIN Numbr/ VAT ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡ ወይም ቲኦቲ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ ያስፈልጋቸዋል።

3ኛ. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ በብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 21 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

4ኛ. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ኦርጅናል ሰነድ እና ፎቶ ኮፒ ሰነድ በተናጠል በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ የድርጅቱ ስም ማህተም ስልክ ቁጥር እና ፊርማ መኖር አለበት። የሚጫረቱበትን የዕቃ አይነት በመጥቀስ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት በስራ ሰአት ሶስተኛ ፎቅ በቢሮ ቁጥር 21 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5ኛ. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህራዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ባበቃ በመጨረሻ ቀን 10፡30 ይታሸግና እና በማግስቱ 3፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

6ኛ. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው እና የጨረታውን አሸናፊ 10% የጨረታው ውል ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

7ኛ. አሸናፊው ተጫራች ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30 እስከ 11፡30 ንብረቶችን በራሱ በመጓጓዝ ማስጫኛና ማውረጃውን ጨምሮ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አሰተዳደር ፅ/ቤት ግቢ ውስጥ ማውረድ ይኖርበታል፡፡

8ኛ. ጽ/ቤቱ የሚያጫርተውን የዕቃ ብዛት 20 ፐርሰንት መቀነስና መጨመር ይችላል፡፡

9ኛ. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጫራቾች ማብራሪያ ማስረጃ በስልክ ቁጥር 0111-22-67-04 እና 0118-12-24-04 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

10ኛ. ማንኛውም ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ማቅረብ የማይችል ከሆነ ገላጭ እስፔስፍኬሽን ማምጣት አለያም እቃውን የሚያሳይ ጥራት ያለው ፎቶ ማምጣት ይኖርባቸዋል።

11ኛ. ለሰራተኛ ካፍቴሪያ አገልግሎት የሚሰጠው ጉ/ክ/ከ/ወ6/ አስተዳደር በሚገኝበት ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የሰራተኞች ክበብ ሆኖ የቤት ኪራይ ወጪ የመብራት እንዲሁም የውሀ ወጪን ጨምሮ በመስርያ ቤቱ የሚሸፈን መሆኑን ያሳውቃል፡፡

 

አድራሻ ፡- ሽሮሜዳ ከስላሴ ቤተክርስቲያን በታች ባለው በግራ በኩል መታጠፈያ 500 ሜትር ገባ ብሎ

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender