የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ A4 የወረቀት አምራች ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ በረጅም ጊዜ ውል ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር SSNT-T551
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ A4 የወረቀት አምራች ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ በረጅም ጊዜ ውል ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በተጠቀሰው ዘርፍ ላይ ቢያንስ ሦስት (3) ዓመት የሠሩ፣ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በመንግሥት ጨረታዎች ለመሳተፍ የሚያግለግል ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ TIN (የግብር መለያ ቁጥር) ያላቸውና በዘርፉ እየሠራ ያለ ማንኛውም ተቋም በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ እየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T551 በሚል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጂውን (Deposit Slip Copy)፣ የጨረታውን ቁጥርና አይነት እንዲሁም የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ ከታች በተጠቀሰው የኢ-ሜይል አድራሻ በመላከ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 120,000.00 (መቶ ሃያ ሺ ብር) በባንከ የተረጋገጠ ቼከ (ሲፒኦ) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው ባንክ ጋራንቲ (unconditional bank guarantee) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ መሠረት የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የስትራቴጂከ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ነሐሴ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፌያ
ፕሮኪዩርመንት እና ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት ክፍል
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
በስልክ ቁጥር 011 517 80 25
ኢ-ሜይል: eskedarya@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
