የጊንር አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን ምግብ የሚያቀርቡ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመስጠት ይፈልጋል፡፡
የጊንር አጠቃላይ ሆስፒታል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጊንር አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን ምግብ የሚያቀርቡ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመስጠት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ቀጥሎ የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች እንዲወዳደሩ እንጋብዛለን፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ያላቸው፤ የግብር መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ስር የተደራጁ ተጫራቶች ቫት ያልተመዘገቡ ከሆነ በገቢዎች ባለሥልጣን ዕውቅና ባለው የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ የሚገለገሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 5,000.00 (አምስት ሺህ) ብር የያዘ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ብር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ኮፒና ኦርጅናል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አቅራቢው ድርጅት ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀለት ከ5ኛው ቀን በኋላ ከ6ኛው ቀን ጀምሮ መ/ቤቱ ቀርቦ ውል መፈራረም ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከተታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 በመክፈል የጊንር አጠቃላይ ሆስፒታል የግዥና ንብረት አስተደዳር ክፍል ቢሮ ቁጥር 09 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመኖር የጨረታ ሰነድ እንዳይከፈት አይከላከልም ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0946319866/0975407902 ደውለው ይጠይቁ።
የጊንር አጠቃላይ ሆስፒታል
