ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለድርጅቱ የተለያዩ አገልግሎቶች ጥቅም ላይ የሚውሉ የተለያዩ የአይቲ እቃዎች እና የተለያዩ ተሽከርካሪ ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
Commercial Nominees Plc (ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ
CN/NCB/04/18
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለድርጅቱ የተለያዩ አገልግሎቶች ጥቅም ላይ የሚውሉ፡-
ሎት 1 - የተለያዩ የአይቲ እቃዎች IT Equipments (Desktop computer, Laptop computer, printer, Heavy duty copy machine, Scanner e.t.c)
ሎት 2 - የተለያዩ ተሽከርካሪ ጎማዎች ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ኢንቨሎፕ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሰዓት 7፡00-11፡00) ማግኘት ይቻላል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ነሀሴ 6 ቀን 2017 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ያሸነፈው ተጫራች የዕቃዎች ርክክብ የሚደረግበት ቦታ ገርጂ የድርጅቱ የዕቃ ግምጃ ቤት ይሆናል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡ ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ሕንፃ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-1-569992
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማሕበር
