አይናጌ ሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት ለ2017/18 በጀት ዓመት ለተማሪዎች በጠቅላላው 16,750 (አስራ ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ) ሲነርላይን ባለ 50 ሉክ ባለመስመር የተለበደ አንደኛ ደረጃ ደብተር መግዛት ይፈልጋል፡፡
አይናጌ ሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት
የተማሪ ደብተር ግዢ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
መቀመጫውን በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን በቅበት ከተማ አስተዳደር ያደረገው አይናጌ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት በመዝገብ ቁጥር 1544 ዳግም ተመዝግቦ ሕጋዊ ፈቃድ ያለው ድርጅት ነው፡፡
ድርጅቱ ለ2017/18 በጀት ዓመት ለተማሪዎች በጠቅላላው 16,750 (አስራ ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ) ሲነርላይን ባለ 50 ሉክ ባለመስመር የተለበደ አንደኛ ደረጃ ደብተር መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ በዘርፉ የተሰማራ ማንኛውም ድርጅት ወይም ግለሰብ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የቫትና የተርን ኦቨር ታክስ ሰርተፊኬት እንዲሁም ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ስራዎችን ሰርቶ የመልካም አፈጻጸም ደብዳቤ ካለና ሌሎች ለጨረታው አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን ማቅረብ የሚችል የጨረታውን ሰነድ (የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ) ከድርጅቱ ዋናው ቢሮ በማይመለስ ብር 700 (ሰባት መቶ ብር ብቻ) ገዝቶ በመሙላት እንዲሁም የሚወዳደርበትን ጠቅላላ ዋጋ ቢያንስ 2 ፐርሰንት CPO በባንክ በተረጋገጠ ጨምሮ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ድርጅቱ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን ጨረታው በ10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ማሳሰቢያ:- አሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ደብተሮቹን በራሱ ትራንስፖርት ድርጅቱ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
አድራሻ፡- ከአዲስ አበባ ወደ ሆሳዕና በሚወስደው መንገድ ላይ ከቡታጅራ 12 ኪሜ ላይ ስልጤ ዞን ቅበት ከተማ
ስልክ ቁጥር:- 046-8-82-01-40/046-8-80-04-40
አይናጌ ሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት
