Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ ለተፈጥሮ ኃብት ዳይሬክቶሬት በ/GCF/ የበጀት ድጋፍ በድርቅ አደጋ ለተጋለጡ ወረዳዎች ማለትም ለእነብሴ ሳርምድር፣ ለታች ጋይንት እና ላስታ ወረዳ አገልግሎት የሚውል የሶላር ሞተር ፓምፕ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ ለተፈጥሮ ኃብት ዳይሬክቶሬት በ/GCF/ የበጀት ድጋፍ በድርቅ አደጋ ለተጋለጡ ወረዳዎች ማለትም ለእነብሴ ሳርምድር፣ ለታች ጋይንት እና ላስታ ወረዳ አገልግሎት የሚውል የሶላር ሞተር ፓምፕ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  1. በዘርፉ የተሰማሩ ሆነው በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከኦሪጅናሉ ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. የሚገዙ የሶላር ፓምፕ ግዥ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ገንዘብ የዋጋውን ጠቅላላ ድምር 1% /አንድ ፐርሰንት/ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ አሰርተው በቢሮው ስም ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ /የመወዳዳሪያ/ ሃሳቡን የቴክኒካል ሰነድ ዋና እና ቅጅ ለየብቻው እና የፋይናሻል ሰነዱ እና የጨረታ ማስከበሪያውን በአንድ ዋና እና ቅጅ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግብርና ቢሮ ግቢ ቢሮ ቁጥር 025 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርበታል።
  9. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች በፎቶ የተደገፈ ናሙና ማቅረብ ግዴታ ሲሆን ሲቀርብም ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር አብሮ መቅረብ ይኖርበታል፤ በተጨማሪም የጨረታ ሰነዱ ዋና እና ቅጅ በሚል ካልመጣ ከውድድር ውጭ የሚደረግ ይሆናል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ በ16ኛው ቀን ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 25 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 2205849 /0583208095/ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት ላይኖረው ይችላል፡፡ ባጋጣሚ የተሰረዘም ከሆነ የሞላው ድርጅት ፊርማ መኖር አለበት፡፡
  14. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ።

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ

 

Save Tender