Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተሸከርካሪ መለዋወጫዎችን ፤ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፤ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

AA Kaliti Customs Office (አ.አ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)


 

በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2018

 

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተሸከርካሪ መለዋወጫዎችን ፤ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፤ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በመሆኑም፡-

  1. በግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርበት ሲሆን ለሃራጅ ጨረታ ደግሞ ከጨረታ አንድ ቀን በፊት ይዞ ማስመዝገብ ይኖርበታል፡፡
  2. በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም፡፡
  3. ተጫራቾች የተሽከርካሪውን እና የዕቃዎቹን የጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. በዕቃ ግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የዕቃ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለዕቃዎች ብር 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በተ.ቁ 4 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት፡፡ ነገር ግን በዕቃ ሐራጅ በጨረታ ሰነድ ላይ በሚገለጹ የተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) መጠን የሚወሰን መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  6. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ፡፡

 

ተ.ቁ

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነዱ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

የዕቃ ሐራጅ

እስከ 28/11/2017

29/11/2017 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል

የዕቃ ግልጽ

እስከ 29/11/2017

30/11/2017 3፡45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል

 

  1. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- ኢአ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
  2. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  3. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል።
  4. ከላይ በተ/ቁ 9 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
  5. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ፡- 011-470 - 85-03

አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ

 

አቃቂ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender