Tender Detail

Tender Details


በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ አልባሳትና ጫማዎች፣ የኮስሞቲክስና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች መገናኛ እና ኮምፒውተር ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ መለዋወጫዎች፤ የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎች፣ እንዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01-2018

 

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ አልባሳትና ጫማዎች፣ የኮስሞቲክስና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች መገናኛ እና ኮምፒውተር ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ መለዋወጫዎች፤ የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎች፣ እንዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ቦታ ጋር በዘርፉ የፀና እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የሚሰጥ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  2. ከላይ በተ/ቁ 1 የተገለጸው ተጫራች ማሟላት ያለበት መስፈርት ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከብር 500ሺህ በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የሚፈልግ ተጫራች ሌሎች የተዘረዘሩ መረጃዎችን ማቅረብ እንዳለ ሆኖ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አይገደድም አያስፈልግም።
  3. ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች እስከ ከሐምሌ 21/2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 28/2017 ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 የዕቃዎችን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ፤
  4. ለግልፅ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች የሚጫረቱ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 28/2017 ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ 6፡00 የዕቃዎችን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ እየከፈሉ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 መግዛት ይችላሉ።
  5. የግልፅ ጨረታው ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡45 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ይከፈታል፣
  6. ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ ለዕቃ የሰጡትን ዋጋ 5% የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲፖዚት አካውንት ቁጥር 1000013088865 ገቢ በማድረግ እና ገቢ ያደረጉበትን የባንክ አድቫይስ ከጨረታ ሰነዱ እና ከሌሎች መረጃዎች ጋር በማያያዝ በፖስታ የተጫራቹን ስም እና አድራሻ በግልጽ በመፃፍ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡45 ድረስ ቢሮ ቁጥር 506 በተዘጋጀው የሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣
  7. በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  8. ያስያዙት ዋስትና ለአሸነፈ ተጫራቾች ከሽያጭ የሚታሰብ ሲሆን በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ጨረታ ውጤት ከተገለጸ በኋላ ባሉት ሶስት የስራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ይሆናል፣
  9. ተጫራቾች በጨረታው ለእቃው ከሚሰጡት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት (15%) የሚጨመር ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በጨረታው ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ 5 /በአምስት/ ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ እና እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፤
  11. ከላይ በተ/ቁ 10 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ማንሳት ያልቻሉ ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘ ዋስትና ለመ/ቤቱ ግቢ ሆኖ እቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል፤
  12. በግልፅ ጨረታ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሳጥኑ ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ፤ ማሻሻል ወይም ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ውጭ ማድረግ አይችልም፤
  13. ለግልፅ ጨረታ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፤
  14. በጨረታ የሚሸጥ ዕቃ በተቋሙ ከመወረሱ በፊት የእቃው አስመጭ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበረ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፤
  15. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ የወጡ ዕቃዎችን ከቅ/ጽ/ቤቱ ሰነድ በመግዛት የወጡ ዕቃዎችን ዝርዝር በመመልከት እንዲሁም በስልክ ቁጥር 058-320-74 18/058 320- 7569 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

አድራሻ፡- በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው ዘመን ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን

 

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህርዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

 

Save Tender