በአርሲ ዞን የዲገሉና ጢጆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጽህፈት መሣሪያና፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ ዕቃዎች፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች፣ የተለያዩ የቴክኒክና ሙያ የስልጠና ዕቃዎች፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት የአርሲ ዞን የዲግሉና ጢጆ ወ/ገ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁ-06/2018
በአርሲ ዞን የዲገሉና ጢጆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጽህፈት መሣሪያና፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ ዕቃዎች፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች፣ የተለያዩ የቴክኒክና ሙያ የስልጠና ዕቃዎች፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡-
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር በመክፈል ያሳደሱ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት (TIN) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርባቸው ዕቃዎች ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ዕቃዎቹን መስሪያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ የሚችል፡፡
- አቅራቢዎች ጠቅላላ ዋጋውን በቁጥርና በፊደል መፃፍ አለባቸው፡፡ በቁጥርና በፊደል የተገለፀው የዋጋ መጠን መካከል አለመጣጣም ካለ በፊደል የተገለፀው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪ በነጠላ ዋጋ እና በጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ ነጠላ ዋጋው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
- ተወዳዳሪዎች ሀሳብ የማቅረቢያው ሰነድ ላይ የዕቃውን አይነት፣ የምርቱን አይነት፣ የተመረተበትን አገር፣ ሞዴል ቁጥሩንና የተመረተበትን ዓ.ም ተጨማሪ ማብራሪያ መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተወዳዳሪዎች ባሸነፉበት ዕቃ ላይ የዕቃውን (ናሙና) ለአንድ ዕቃ አንድ ሳምፕል ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አቅራቢዎች በእያንዳንዱ የዕቃ ዝርዝር ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ውስጥ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋውን እንዲሁም ቀን፣ ፊርማና የድርጅቱን ማሕተም ማስፈር ይገባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የግዥ መጠኑን በ20% ያህል መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምር ከዲ/ጢጆ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 ዘወትር በስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ ለጽህፈት መሣሪያዎች፤ ለመኪና ጎማዎች እና ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር ዕቃዎች ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ) ፤ እንዲሁም፤ ለጽዳት ዕቃዎች ፣ እና የቴክኒክና ሙያ የስልጠና ዕቃዎች እያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ፤ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳችሁን ፋይናንሻል ዶክመንት ኦሪጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንት ኦሪጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች አሸናፊ መሆኑ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ 10 ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ውል መቀበል አለበት
- አሸናፊው ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት የጨረታውን ሰነድ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ከ4፡00 ሰዓት በኋላ የጨረታው ሳጥን ስለሚዘጋ በሰዓቱ ያልተገኘውን ተጫራች የማናወዳድር መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ጨረታው በዚሁ እለት ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ቀኑ ዓመት በዓል ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፦ በስልክ ቁጥር፡-022-338-00-14/0910001453 ይደውሉ፡፡
በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት የአርሲ ዞን የዲግሉና ጢጆ ወ/ገ/ጽ/ቤት
