Tender Detail

Tender Details

  • Company Belayab Motors (በላይአብ ሞተርስ ኃ.የተ.የግል ማህበር)
  • Address ቃሊቲ ብሔራዊ ት/ቤት ጀርባ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114 343691
  • Websitehttps://www.belayabmotors.com
  • Deadline06 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security50000.00
  • opening date2025-08-07 00:00:00
  • Categories Vehicle Spare Parts

በላይአብ ሞተርስ ኃ.የተ.የግል ማህበር የኪያ (KIA Spare parts) የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Belayab Motors (በላይአብ ሞተርስ ኃ.የተ.የግል ማህበር)


 

የመለዋወጫ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በላይአብ ሞተርስ ኃ.የተ.የግል ማህበር የኪያ (KIA Spare parts) የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ እቃዎቹ አዲስ አበባ እና አዳማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ይገኛሉ፡፡

ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

  1. የጫረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመግዛት ዋጋቸውን በመሙላት ለጫረታው በተዘጋጀው ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  2. ጨረታው የሚቆየው ጋዜጣው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ሲሆን በ11ኛው ቀን 4፡00 ተከፍቶ 4፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሳሪስ ቀይመስቀል ውስጥ በሚገኘው በላይአብ ሞተርስ ይከፈታል፡፡
  3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የተለያዩ መለዋወጫ እቃዎች ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ድርጅቱ ባወጣው የመነሻ ዋጋ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ሰነድ ከገዙ በኋላ ቃሊቲ ብሔራዊ ት/ቤት ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በመቅረብ የእቃዎቹን ናሙና በአካል ማየት ይችላሉ፡፡
  6. አሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከፍሎ በ15 ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የሚፈልገውን የመለዋወጫ ብዛት በተናጠል መጫረት ይችላል፡፡
  9. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

ከላይ በተዘረዘሩት መስፈርት ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች ሰነዱን ሳሪስ ካዲስኮ ዋና መስሪያቤት የበላይአብ ሞተርስ ግቢ ውስጥ መውሰድ ይችላሉ፡፡

አድራሻ

በላይአብ ሞተርስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

ሞባይል :- 0966 21 51 83/84

ስልክ፡- 0114 343691

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

 

Save Tender