Tender Detail

Tender Details


በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ት/ፅ/ቤት ስር የሚገኘው ለሰላም በር ቅ/አ/ና/የመጀ/ና/መ/ደ/ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመሠረተ ልማት፤ በውስጥ ገቢና በመደበኛ በጀት ሎት 1 የተለያዩ ኬሚካሎችና የሚወገዱ ንብረቶች ሎት.2 ሜዳ ማስተካከል ስራ ሎት.3 በር ፣ ዴክስና የG+4 ቀለም ቅብ ጥገና ስራ ሎት.4 የቢሮች እድሳትና ጥገና ስራ ሎት.5 የውሃ መስመር እድሳትና ጥገና ስራ ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ስራ ተቋራጮችን አወዳድሮ በአሸናፊው ድርጅት ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ሠላም በር ቅድመ አንደኛ፣ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


 

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ መመሪያ መ.ቁ.01/18

 

በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ት/ፅ/ቤት ስር የሚገኘው ለሰላም በር ቅ/አ/ና/የመጀ/ና/መ/ደ/ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመሠረተ ልማት፤ በውስጥ ገቢና በመደበኛ በጀት ሎት 1 የተለያዩ ኬሚካሎችና የሚወገዱ ንብረቶች ሎት.2 ሜዳ ማስተካከል ስራ ሎት.3 በር ፣ ዴክስና የG+4 ቀለም ቅብ ጥገና ስራ ሎት.4 የቢሮች እድሳትና ጥገና ስራ ሎት.5 የውሃ መስመር እድሳትና ጥገና ስራ ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ስራ ተቋራጮችን አወዳድሮ በአሸናፊው ድርጅት ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሠ የንግድ ፍቃድ መሆኑን የሚገልፅ አግባብነት ያለው ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። በተጨማሪ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ህጋዊ ሰነዱች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

  1. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ በሰላም በር ቅ/አ/ና/የመጀ/ና/መደ/ት/ቤት ክፍያና ሂሳብ አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት (ቢሮ ቁጥር 6) በመቅረብ የማይመለስ 200 ብር /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 7 የስራ ቀናት በአየር ላይ ወሎ በ8ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ በ8ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት ከቀኑ 4፡30 ይከፈታል የጨረታ መስፈርቱን ያሟሉ ተጫራቾች በእለቱም ባይገኙም ፖስታቸው ይከፈታል።
  2. ተጫራቾች ከጨረታ ሠነዳቸው ጋር ተዛማጅና ተያያዥነት ባላቸው ስራዎች ከመንግስት ተቋማት ቢያንስ አራት ዓመት የሰሯቸው የመልካም አፈፃፀም የምስክር ወረቀት (ደብዳቤ) አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ የሚያቀርቡት የስራ አይነት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ የሌለበት፣ ስልጣን ባለው አካል የተፈረመባቸው የተሟላ አድራሻቸውን የሚገልጽና ህጋዊ ማህተም ያረፈበት ሊሆን ይኖርበታል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት1. የተለያዩ ኬሚካሎችና የሚወገዱ ንብረቶች 5000. ሎት2. ሜዳ ማስተካከል ስራ 16000 ሎት3. በር፣ ዴክስና የG+4 ቀለም ቅብ ጥገና ስራ 10000 ሎት 4. የቢሮች እድሳትና ጥገና ስራ. 7000 ሎት.5 የውሃ መስመር እድሳትና ጥገና ስራ 2000, በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ በት/ቤቱ ስም በማሰራት ከጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሠዓት በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. ተራff ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ዋጋ ላይ የዋጋ ለውጥም ሆነ ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም።

በተወዳደሩት ዋጋ አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ በ5 ቀናት ውስጥ ቀርበው የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ በት/ቤቱ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

  1. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለጸበት በ5 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል ካልተዋዋለ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
  2. አሸናፊ ተጫራች በስፔስፍኬሽኑ መሰረት ስራው የሚጠቀምባቸው ማተሪያሎች የጥራት ደረጃ ት/ቤቱ በመደበው ባለሙያ የጥራት ደረጃቸው ሲረጋገጥ ብቻ ነው ወደ ስራው መግባት የሚችሉት።
  3. ት/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች ከመረጠ በኋላ በሚያሰራው ግንባታ 30% የመቀነስም እንዲሁም የመጨመርም መብቱ የተጠበቀ

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ሠላም በር ቅድመ እንደኛ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

  1. ተጫራቾች የግንባታ ሂደቱን የሚያከናውኑት ት/ቤቱ በሚያቀረበው ዲዛይን መሰረት ብቻ ነው።
  2. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  3. በጨረታው ሰነድ ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዮች ካሉ በአካል በመቅረብ ሠላም በር ቅድመ አንደኛ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ግዥ ቢሮ መጠየቅ ይችላሉ።
  4. ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ሲሞላ 15% ቫትን በመጨመር ይሆናል። 5% ቫትን ያላካተተ ተጫራች ለውድድር አይቀርብም፡፡
  5. ተጫራቾች የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገቡበትን ፎርማትን በመሙላት የተጫራቹን ድርጅት ፈርማና ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡

አድራሻ፡- በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ሉካንዳ ታክሲ ማዞሪያ ወደ ፌደራል ፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም በሚወስደው አስፓልት በስተቀኝ በኩል ሰዋሰው ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ጎን

 

በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ሠላም በር ቅድመ አንደኛ፣ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

 

Save Tender