Tender Detail

Tender Details

  • Deadline09 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security2.00
  • opening date2025-08-09 00:00:00
  • Categories Transportation Service And Cargo

በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ባ/ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለሰራተኞች ጠዋት እና ማታ ከቤት ወደ ስራ ቦታ እና ከስራ ቦታ ወደ ቤት ለማጓጓዝ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመግዛት ስለሚፈለግ በዘርፉ ከተሰማሩ አካላት ማለትም /71113/ የንግድ ስራ ፈቃድ የየብስና ተዛማጅ አገልግሎት ሆኖ ሊብሬው ለንግድ የሚል እና /71112/ የንግድ ስራ ፈቃድ ሃገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሆኖ ሊብሬው የመኪና ማከራየት የሚል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2018

 

በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ባ/ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለሰራተኞች ጠዋት እና ማታ ከቤት ወደ ስራ ቦታ እና ከስራ ቦታ ወደ ቤት ለማጓጓዝ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመግዛት ስለሚፈለግ በዘርፉ ከተሰማሩ አካላት ማለትም /71113/ የንግድ ስራ ፈቃድ የየብስና ተዛማጅ አገልግሎት ሆኖ ሊብሬው ለንግድ የሚል እና /71112/ የንግድ ስራ ፈቃድ ሃገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሆኖ ሊብሬው የመኪና ማከራየት የሚል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች /ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተጠየቁትን መስፈርቶችና ግዴታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደስ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የባለቤትነት ማስረጃ ወይም ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር መክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያርጋግጥ በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንክ በተመሰከረለች ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 03 አልካን ኮሌጅ ጎን ከሚገኘው ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በጥንቃቄ በመሙላትና በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ/ በማሸግና በዋጋ ሙያው ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በግልጽ በማስቀመጥ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የግዥ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 307 ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል ነገር ግን 16ኛው ቀን በዓል፣ እሁድ ከሆነ 17ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
  7. የጨረታ አሸናፊው የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና 10% በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የአመቱን በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል፡፡
  8. መ/ቤቱ በጨረታው የተገለፀውን አገልግሎት ብዛት እንዲገዛ አይገደድም፡፡
  9. ተጫራቾች የሚሞሉትን ሰነድና ሌሎች ማስረጃዎች ኦርጅናል /ዋና/ እና /ኮፒ/ ቅጅ ለየብቻ በማሸግ በድጋሜ በአንድ ፖስታ ሁለቱን በማሸግ ከተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  10. ከትራንስፖርት አገልግሎት ክፍያ ውጭ ማንኛውንም ወጭ ተቋሙ የማይሸፍን መሆኑን (የነዳጅ፣ የሹፌር እና የመኪና ብልሽት) መገንዘብ ይጠበቅባቸዋል።
  11. ተቋሙ የሚፈልገው የትራንስፖርት አገልግሎት ሲሆን አገልግሎቱ ጠዋት የመግቢያ የስራ ስዓት እና ምሽት የስራ ሰዓት መውጫ ብቻ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ተጫራቾች አንድ ሊብሬ/ መኪና ከአንድ የጉዞ መስመር በላይ መጫረት የማይችሉ መሆኑን ማወቅ ይገባቸዋል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 058-226-34-01 / 058-226-33-21 መደበኛ የጨረታው ሰነድ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ በገቢዎች ሚኒስቴር ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት የተዘጋጀ 2017 ዓ.ም

 

በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ባ/ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

 

Save Tender